የሴቶች ኮከስ

1/ የሴቶች እና ህፃናት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ተግባርና ኃላፊነት እንደተጠበቀ ሆኖ የሴቶች ኮከስ የሚከተሉት ተግባራት

ይኖሩታል፦

) የሴት የምክር ቤት አባላት የልምድ ልውውጥ ያካሄዳል፤

) የሴቶች መብትና ተጠቃሚነትን በሚመለከቱ የተለያዩ አጀንዳዎች ምክክር ያካሄዳል፤

) የአቅም ግንባታና የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን ያከናውናል፤

) ከክልል ሴቶች ኮከሶች ጋር ግንኙነት ያደርጋል።

2/ የሴቶች ኮከስ ተጠሪነት ለአፈጉባዔው ይሆናል፣ የኮከሱ ዝርዝር አደረጃጀትና አሰራር በዚህ ደንብ መሰረት በሚወጣ

መመሪያ ይወሰናል።

  • Responsive Image
  • Responsive Image

null Women parliamentarian caucus evaluated its 6th month performance.

የሴቶችን ተሣታፊነትና ተጠቃሚነት በየደረጃው ለማረጋገጥ በተላይ በዩኒቨርሲቲዎች አከባቢ ለሴት ተማሪዎች ምቹ ሁኔታዎችን ከመፍጠር አኳያ ሁሉም ማህበረሰብ የራሱን ኃላፊነት መወጣት እንደላባቸው ተገለጸ፡፡

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተመራጭ ሴቶች ኮከስ የ2010 በጀት አመት በተደረገው የአፈ-ጉባኤዎች መድረክ ጎን ለጎን የ6 ወራት የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርትን በቢሾፍቱ ከተማ ገምግሟል፡፡

በዚህ ወቅትም የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ-ጉባኤ እና በምክር ቤቱ የኮከስ ሰብሳቢ የተከበሩ ወ/ሮ ሽታዬ ምናለ እንዳሉት ዩኒቨርሲቲዎች አንዱ ስራቸው በማህበረሰብ አገልግሎት ላይ በተለያዩ መልኩ ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር በመቀናጀት አካባቢውን የማልማትና በተለይ የሰው ሃይሉ ላይ ይበልጥ መስራት እንደለባቸው ጠቁመዋል፡፡ 

አያይዘውም በየዩኒቨርሲቲዎቹ ለሚማሩ ሴት ተማሪዎች ላለባቸው ተፈጥሮዊ ምክንያቶች ምቹ ሁኔታዎች ሊፈጠርላቸው እንደሚገባ፣ በተቋሙ አካባቢ የሚደረጉት የተለያዩ የንግድ ሥራዎችም የህግ ማዕቀፍ ሊኖራቸው እና ሁሉም ማህበረሰብ፣ ወላጆችና የሃይማኖት አባቶችን ጨምሮ በተለያዩ መልኩ በሴቶች ላይ ለሚደርሱት ጫናዎች የበኩላቸው አስተዋጽኦ መወጣት እንደለባቸውም አሳስበዋል፡፡

በሌላ በኩልም በክልሎች እየተከናወኑ ስለሚገኙ የሴቶች ኮካስ (ፎረም) ተግባራት በበጀት ዓመቱ በተመረጡት 3 ክልሎች በትግራይ፣ በደቡብ ብሔር ብሄረሰቦችና ህዝቦች እና በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል በፖለቲካው፣ በኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ዘርፎች የሴቶች ተጠቃሚነትና ተሳታፊነትን አኳያ ያለውን ሁኔታ ለመመልከት የመስክ ምልክታ መደረጉ ተገልጿል፡፡

በጉብኝቱ ወቅትም በየደረጃው ያሉ አመራሮች የሴቶችን አደረጃጀቶችን ለማጠናከር የሚሰሩትን ስራዎችንና የተገኙትን የተለያዩ ልምዶችን በመቀመር ሰፊ ውይይት በማድረግ በቀጣይም በየክልሎቻቸው እንደሚሰሩበት በቀረበው ሪፖርት ተመላክቷል፡፡