null Branch media institutions at Bahirdar city are facing accessibility due to shortage of budget and material ball ups.

በባህርዳር ከተማ የሚገኙ ቅርንጫፍ የሚዲያ ተቋማት በማቴሪያል ብልሽት እና በበጀት እጥረት ምክንያት የተደራሽ ውስንነት እንዳለባቸው ተገለጸ፡፡

በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የህግ፣ፍትህና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ባደረገው የመስክ ምልከታ በኢትዮጵያ ብሮድካስት ባህርዳር ቅርንጫፍ ራዲዮ እና ቴለቭዥን ስርጭት ጉብኝት አድርጓል፡፡

በተመሳሳይም ቋሚ ኮሚቴው በኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ድርጅት ባህርዳር ቅርንጫፍ እና በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አቀፍ የራዲዮና የቴሌቭዥን ስቲዲዮ ግንባታዎችን ተዘዋውሮ ጎብኝቷል፡፡

ቋሚ ኮሚቴው ጉብኝት ባደረገበት ወቅት የትዮጵያ ብሮድካስት የባህርዳር ቅርንጫፍ ራዲዮ ማሰራጫ ጣቢያው በማቴሪያል ብልሽት፣በመንገድ ፕላን እና በሌሎች ተያያዥ ምክንያቶች ስርጭት ማቆሙን ተገንዝቧል፡፡

በ2011 በጀት ዓመት ተቋሙ ገቢውን ለማሳደግ ከቴሌቭዥን ተጠቃሚዎች 1.5 ሚሊየን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ 450 ሺህ ብር ብቻ የሰበሰበ ሲሆን አፈፃፀሙም ዝቅተኛ እንደሁነ ቋሚ ኮሚቴው ገምግሟል፡፡

የቅርንጫፉ ሰራተኞች በበኩላቸው ለተቋሙ ገቢ ማሳደጊያ የተሰበሰበው ገንዘብ ዝቅተኛ የሆነነበት ምክንያት ህብረተሰቡ ከግንዛቤ ማነስ አንጻር የመክፈል ፍላጎት እንደሌለው ገልጸው ቤት ለቤት እየዞሩ ለማስከፈል ጥረት ቢደረግም አመርቂ ውጤት ማምጣት እንዳልተቻለ ተናግረዋል፡፡

የመረጃ ጥራትና ተደራሽነትን በተመለከተም በአንቴና ለሚጠቀሙ ግለሰቦች እንጂ ለሁሉም ማህበረሰብ ተደራሽ ያልሆነው የቴሌቭዥን ስርጭት የምስልና የድምፅ ጥራት ችግር እንዳለበትም በቅንጫፉ የሚሰሩ ባለሙያዎች ተናግረዋል፡፡

የተቋሙ ሰራተኞች አክለውም ከደረጃ እድገት፣ ከደመወዝና ጥቅማጥቅም አንጻር ቅሬታ እንዳላቸው ለቋሚ ኮሚቴው ገልጸዋል፡፡

ቋሚኮ ሚቴው የባህርዳር ዩኒቨርስቲን የማህበረሰብ አቀፍ የራዲዮና ቴሌቭዥን ስትዲዮ ግንባታዎችን የጎበኘ ሲሆን የግንባታ ሂደቱ በመጠናቀቅ ላይ እንደሚገኝ እና በቅርቡተጨማሪ 28 ጋዜጠኞች ተቀጥረው ስራ የሚጀምር መሆኑን ተገንዝቧል፡፡

በተመሳሳይም ቋሚ ኮሚቴው በኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ድርጅት ባህር ዳር ቅርንጫፍ ጉብኝት ባደረገበት ወቅት የቅርንጫፍ መስሪያ ቤቱ ሰራተኞች ከደረጃ መዋቅር፣ ከተሽከርካሪ፣ ከደመወዝና ከጥቅማጥቅም ክፍያ አንፃር ችግሮች አንዳሉባቸው ተረድቶ ከዋና መሰሪያ ቤቱ ጋር ተነጋግሮ ችግሮችን ለመቅረፍ ጥረት የሚደረግ መሆኑን እና በቀጣይም አማራጭ መፍትሔዎች የሚፈለጉ እንደሆነ ለቅርጫፉ ስራተኞች አሳስቧል፡፡