null Committee of the House announced that the Ethiopian Meat and Dairy Industry Development Institute are limited in expanding its export destinations.

የኢትዮጵያ ስጋና ወተት ኢንደስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት  የኤክስፖርት መዳረሻ ሃገራትን በማስፋት ረገድ ውስንነት እንዳለበት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት  የንግድና ኢንዱስትሪ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አሳወቀ፡፡

መጋቢት 25/2011 ዓም፤   ቋሚ ኮሚቴው   የኢንስቲትዩቱን   የ 2011 በጀት አመት የስምንት  ወራት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ገምግሟል፡፡

የኢትዮጵያ ስጋና ወተት ኢንደስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት  ሃገሪቱ ከኢንስቲትዩቱ የምትፈልገውን የውጭ ምንዛሬ ለማግኘት የተደራሽነት አድማሱን በማስፋት ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ አድርጎ መጓዝ እንዳለበት  በምክር ቤቱ የንግድና ኢንዱስትሪ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ጌታቸው መለሰ ጠቁመዋል፡፡

በአሁኑ ጊዜ የኢንስቲትዩቱ  የኤክስፖርት መዳረሻ ሃገራት የተባበሩት አረብ ኤምሬቶችና ሳዉዲ አረቢያ ብቻ  መሆናቸውንም አቶ ጌታቸው ገልጸዋል፡፡

ኢንስቲትዩቱ  ለፈጻሚዎቹ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች መስጠት መቻሉ ፣ የተገልጋይ እርካታን ለመመዘን ጥረት መደረጉ ፣ የሃገር ውስጥ ባለሃብቶች በኤክስፖርት በኩል ትልቁን ድርሻ እንዲወስዱ መደረጉ፣ አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርኮች የተሻለ ስራ እንዲሰሩ  የተደረገው ጥረት አበረታች መሆኑን የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ ጌታቸው መለሰ ተናግረዋል፡፡

በሌላ በኩል የመልካም አስተዳደር እቅድ ራሱን ችሎ አለመታቀዱ፣ ሴክተር ተሸጋሪ ስራዎች ላይ አርብቶ አደሩን ያማከለ ስራ  አለመሰራቱ፣  ምርትና ምርታማነትን ለመጨመር ካይዘን ላይ   አለመሰራቱ፣ በቆዳና ሌጦ ጥራት ረገድ በአግባቡ  ኢንስቲትዩቱ በትኩረት አለመስራቱን  አቶ ጌታቸው በእጥረት ከጠቀሷቸው መካከል ይገኙበታል፡፡

የኢንስቲትዩቱ የስራ ኃላፊዎች በበኩላቸው በቋሚ ኮሚቴው  በኩል በቀጣይ ትኩረት ያሻቸዋል ተብለው በተለዩ ነጥቦች ላይ ኢንስቲትዩቱ  የተሻለ ስራ እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡