null Dr. Aklilu meets Ethiopia’s Honorary Consul

የውስጥና የውጭ አገር ቱሪስቶች ስለ አገሪቱ ታሪክና ባህል ግንዛቤ እንዲኖራቸው ቅርሶችን በቋሚና ጊዜያዊ ኤግዚቢሽን አደራጅቶ ለእይታ እንዲውሉ በታቀደው መሰረት ከአውሮፓ ህብረት የባህል ለልማት ፕሮጀክት ጋር በመተባበር የሰው ዘር ምንጭ ሙዝየም የህንፃ ዲዛይን ስራው ሰፊ ውይይት ተደርጎበት ርክክብ እንደተፈጸም ሚኒስትሯ ተናግረዋል፡፡

በህገ-ወጥ መንገድ በግለሰቦች ሲዘዋወሩ የተገኙ 100 የብራና መጽሃፍትን እና 200 የኢትኖግራፊና ታሪካዊ ቅርሶችን ከፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን፣ ከገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ጋር በመተባበር ቅርሶቹ ወደ ባለስልጣኑ የቅርስ ስብስብ ክፍል ውስጥ እንዲገቡ መደረጋቸውንም አክለዋል፡፡

የውጭ ቱሪስት ፍሰት ጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣ ሲሆን በግማሽ ዓመት ውስጥ 485ሺህ 806 የውጭ ዜጎች አገሪቷን እንደጎበኙና ከዘርፉም 1 ቢሊየን 818 ሚሊየን 857 ሺህ 664 ዶላር ገቢ መገኘቱን ሚኒስትሯ በሪፖርታቸው ገልፀዋል፡፡