null Tagesse Chafo, speaker of the House discussed with Trevor Colin Mallard on diplomatic bilateral issues.

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተከበሩ አቶ ታገሰ ጫፎ የኒውዝላንድ አቻቸውን ትሬቨር ማላርድን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ፡፡

ሚያዝያ 07 ቀን 2011 ዓ.ም በውይይቱም ወቅት ኢትዮጵያ እና ኒውዝርላንድ የሁለትዮሽ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር እንደሚሰሩ የሁለቱ አገር አፈ-ጉባኤዎች መክረዋል፡፡

የኒውዝላንድ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ልኡካን ቡድን ከኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጋር የእርስ በርስ ፓርላመንታዊ ግንኙነቱን ለማጠናከር እና የልምድ ልውውጥ ለመቅሰም እንደመጣም ተነግሯል፡፡

የኒውዝላንድ ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ ትሬቨር ማላርድ ኢትዮጵያ እያካሄደች ያለውን ሁለንተናዊ ለውጥ አድንቀው አገራቸው ይህንን ለውጥ እንደምትደግፍ ገልጸዋል፡፡

መጋቢት 01 ቀን 2011 ዓ/ም በተከሰከሰው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የሆነው ET-302-max-800 ህይወታቸውን ላጡ ቤተሰቦች ሀዘናቸውንም ገልጸዋል፡፡

የተከበሩ አፈ-ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ በበኩላቸው ለውጡ ግቡን እንዲመታ የአቻ እህት አገራት ድጋፍ እንደሚያስፈልግና የኒውዝላንድ መንግስትም ይህንን ለማድረግ ያሳየውን አጋርነት አድንቀዋል፡፡

አፈ-ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎም የኒውዝርላንድ ባለሀብቶች መዋዕለ ንዋያቸውን በኢትዮጵያ እንዲያውሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ በኢትዮጵያ የኒውዝላንድ አምባሳደርም ይህንን ጥሪ ወደ ላቀ ደረጃ እንደሚያደርሱት ያላቸውን እምነት ገልጸዋል፡፡

የሁለቱ አገራት አፈ-ጉባኤዎች በተለይ በፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ ዘርፎች እና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ሰፊ ውይይት አድርገዋል፡፡

በትምህርት ዘርፍ በተለይ የሴቶችን ተሳትፎ ለማጠናከር ኒውዝላንድ ድጋፍ ማድረግ እንደምትፈልግ በውይይቱ ተነስቷል፡፡

በፖለቲካው በኩልም ኢትዮጵያ ከጎረቤት አገራት ጋር ያላትን መልካም ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እና በምስራቅ አፍሪካ ሰላምና መረጋጋትን በዘላቂነት ለማስፈን ቁርጠኛ መሆኗን አፈ-ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ ለልዑካን ቡድኑ አስረድተዋል፡፡