null Ethiopian construction Works Corporation should focus on the dillaynce of the costruction sctor.

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን በህንጻ ግንባታ ዙሪያ የሚታይበትን መጓተት በመቅረፍ በዘርፉ የተሰጠውን ሀገራዊ ሀላፊነት መወጣት እንዳለበት የገቢ፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዎች ቋሚ ኮሚቴ ገለጸ፡፡

ሚያዚያ 07 ቀን 2011 ዓ.ም ቋሚ ኮሚቴው ከመንግስታዊ የልማት ድርጅቶች አንዱ በሆነው የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን የመስክ ምልከታ አድርጓል፡፡ በኮርፖሬሽኑ በመገንባት ላያሉትን አዲስ አበባ የመለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ እና የእስልምና ጉዳዮች ጽ/ቤትን እንዲሁም ቃሊቲ የሚገኘውን የኮንስትራክሽን መሳያዎች ማምረቻን ተዟዙሮ ተመልክቷል፡፡

በኮርፖሬሽኑ ቁልፍ ተግባራት አፈጻፀምና ባጋጠሙ ችግሮች ዙሪያም ከኤጀንሲው የስራ ሀላፊዎችና ሰራተኞች ጋርም ተወያይቷል፡፡

በውይይቱም የኮርፖሬሽኑ የቢዝነስ ዴቨሎፕመንት መምሪያ ስራ አስኪያጅ አቶ አዋሽ አብተው ኮርፖሪሽኑ በዋናነት በህንጻ፣ በድልድይ፣ በአሮፕላን ማረፊያ፣ በባቡር መንገዶች፣ በወደብ ግንባታዎች፣ በመስኖና ውሀ ሀይል ማመንጫ፣ በኮንስትራክሽን መሳሪያዎች፣ በህንጻ አካላት ማምረት ላይ በዋናነት በመሰማራት እንዱሁም በማህበራዊ ሃላፊነቶች ስራዎችን በመስራት ሀገራዊ ሀላፊነቱን እየተወጣ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ አዳዲስ የጥናት ኢንቨስትመንት ስራዎችን በመስራት በዘረፉ አገሪቱን ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰራም ነው ብለዋል፡፡

በሌላ በኩል የመሳሪዎች ብልሽትና አቅርቦት፣ የፀጥታና የወሰን ማስከበር፣ የዲዛይን ችግር፣ የውጭ ምንዛሪ፣ የስራ ማስኬጃ ካፒታል እጥረትና ለተሰሩ ፕሮጀክቶች የክፍያ መዘግየት መኖሩን በችግርነት አንስተዋለል፡፡ በኮርፖሬሽኑ የተዘጋጁ የውሀ ግድቦች ቢኖሩም የውሀ ታሪፍ ረቂቅ አዋጅ በመንግስት ፀድቆ ሥራ ላይ ባለመዋሉ ኮርፖሬሽኑ መቸገሩን ገልጸው፣ ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት ም/ቤቱና መንግስት ተገቢውን ትኩረት ሊሰጡት እንደሚገባም ጠይቀዋል፡፡

የቋሚ ኮሚቴው አባላት በኮርፖሬሽኑ በመገንባት ላይ ያሉትን አዲስ አበባ የመለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ እና የእስልምና ጉዳዮች ጽ/ቤትን በአካል በመገኘት ተመልክተዋል፡፡

በተመሳሳይም የኮንስትራክሽን መሳያዎች ማምረቻ ድርጅትን የማምረት ሂደትን ጎብኝተዋል፤ ሰራተኞችንም አነጋግረዋል፡፡

በመጨረሻም የቋሚ ኮሚቴው ንዑሳን ቡድን ሰብሳቢ የሆኑት የተከበሩ ወ/ሮ ናፈቁሽ ደሴና የተከበሩ አቶ መስፍን መሸሻ የመስክ ምልከታውን አስመልክቶ ለኮርፖሩሽኑ የስራ ሃላፊዎች ግብረ መልስ ሰጥተዋል፡፡

ኮርፖሬሽኑ እያከናወነ ያለው ትልልቅ አገራዊ ፕሮጀክቶች አፈፃጸም በጥሩ ሁኔታ ላይ ያሉና አትራፊ መሆኑን በጥሩነት አንስተዋል፡፡

በሌላ በኩል በፕሮጀክቶች አፈፃጸም ላይ መዘግየት መኖሩን፣ ለአብነት የመለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚና የእስልምና ጉዳዮች ጽ/ቤት ህንፃ ግንባታ በቀመጠው የጊዜ ገደብ አለመጠናቁን በአብነት አስቀምጠዋል፡፡ የሰራተኛ ደህንነት መጠበቂያ አለመሟላትና ለገበያ ተደራሽ ያለመሆኑን በእጥረት ካነሷቸው መካከል ይጠቀሳሉ፡፡    

በቀጣይ ከውጪ የሚገቡ የግንባታ መሳሪዎችን በአገር ውስጥ በማምረት የውጪ ምንዛሪን ማዳን፣ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር የወሰን ማስከበርና የይዞታ ማረጋገጫ ችግሮችን መፍታት፣ የውሀ ታሪፍ ረቂቅ አዋጅ ፀድቆ ተግባራዊ የሚደረግበትን መንገድ ማመቻቸት እንደሚገባ ቋሚ ኮሚቴው አሳስቦ የኮርፖሬሽኑ ችግሮች ተቀርፈው በአገሪቱ የግንባታ ሂደት የአንበሳውን ድርሻ እንዲወጣ ቋሚ ኮሚቴውና ም/ቤቱ ተገቢውን ድጋፍ እንደሚያደርጉም ነው የተገለጸው፡፡