null Ethiopian Human right commission candidate commissioner suggestion period become public.

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት እጩ ኮሚሽነር የጥቆማ ጊዜ ይፋ ሆነ፡፡

የካቲት 25/2011 ዓ.ም፤ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን እጩ ዋና ኮሚሽነር አቅራቢ ኮሚቴ   ባካሄደው ስብሰባ ተጠቋሚዎች የሚለዩባቸውን  መመዘኛ መስፈርቶችና የጥቆማ ጊዜ  ይፋ አድርጓል፡፡

በዚህም መሰረት ለኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት እጩ ኮሚሽነር  የጥቆማ  ማቅረቢያ ጊዜ ከመጋቢት 1/07/2011ዓ.ም እስከ መጋቢት 20/07/2011ዓ.ም ድረስ በስራ ስዓት መሆኑን  የእጩ ኮሚሽነር አቅራቢ ኮሚቴው  አባላት ዋና ጸሃፊ ዶ/ር ተመስገን  ባይሳ ገልጸዋል፡፡

የእጩ ኮሚሽነር መመዘኛ መስፈርቶች ማለትም የስራ ልምዶች፣ የትምህርት አይነቶች በቅርብ ቀን በጋዜጣ ታትመው ለህዝቡ ይፋ  የሚደረግ ይሆናል፡፡

መመዘኛዎቹ በአዋጅ ቁጥር 210/1992 አንቀጽ 12 ላይ በተመለከተው መሰረት የሚከናዎኑ ሲሆን፤ የእጩ ኮሚሽነር አቅራቢ ኮሚቴው አባላት  በቀረበላቸው  የመነሻ ጽሁፍ ላይ  ተወያይተውና የመመዘኛ መስፈርቱን በጥልቀት በማየት ከአዋጁ ጋር በማያያዝ  መወሰኑ  ታውቋል፡፡

የሚተካው እጩ ኮሚሽነር ምን አይነት የትምህርት ደረጃ፣ የሙያ መስክ ና የስራ ልምድ ሊኖረው እንደሚገባ  በመነሻ ጽሁፉ ቀርቦ  ውይይት ተደርጎበት ጸድቋል፡፡

ጊዜው የሚፈልገውን ኮሚሽነር  በአግባቡ ለመምረጥ  እንዲቻል ለህዝቡ የተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን ዘዴዎች በመጠቀም  ተከታታይነት ባለው መልኩ  ግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች እንደሚሰራ ዋና ጸሃፊው ተናግረዋል፡፡

ጊዜው የሚፈልገውን ኮሚሽነር ለመተካት ህዝቡ ከተጠቀሰው ቀን ጀምሮ ጥቆማውን አጠናክሮ እንዲቀጥል ዶ/ር ተመስገን ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡

ጠቋሚዎች ጥቆማቸውን ለኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት እጩ ኮሚሽነር አቅራቢ ኮሚቴ በሚከተሉት ዘዴዎች  ማቅረብ ይችላሉ፡፡

 

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን እጩ ዋና ኮሚሽነር አቅራቢ ኮሚቴ ለማቋቋም የቀረበውን የውሳኔ ሃሳብ ማጽደቁ ይታወሳል፡፡