null Federal Integrated Infrastructure Development Coordinating Agency should work with stakehoders.

የፌደራል የተቀናጀ መሰረተ ልማቶች ማስተባበሪያ  ኤጀንሲ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተቀናጅቶ በመስራት በአዋጅ የተሰጠውን ስልጣንና ሀላፊትነት በአግባቡ መወጣት እንዳለበት የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ጉዳች ቋሚ ኮሚቴ አሳሰበ፡፡      

መጋቢት 27 ቀን 2011 ዓ.ም ቋሚ ኮሚቴው በኤጀንሲው በአካል በመገኘት የመስክ ምልከታ አድርጓል፡፡ በምልከታውም በኤጀንሲው ቁልፍ ተግባራት አፈፃጸም፣ በለውጥ ትግበራ፣ በበጀት አፈፃጸም፣ በሴቶችና ህፃናት እንዲሁም በቅንጅታዊ አሰራሮች ዙሪያ የኤጀንውን የስራ ሀላፊዎችና ሰራተኞችን አወያይቷ፡፡

በውይይቱ ወቅትም ኤጀንሲው የዜጎች ቻርተርን አዘጋጅቶ እንዲፀድቅ ለሚመለከተው አካል ማቅረቡን፣ በ55 ፕሮጀክቶች ላይ ተገቢው ክትትል መደረጉን፣ የመልካም አስተዳደርና ኪራይ ሰብሳቢነት ማምከኛ ዕቅድ መዘጋጀቱን፣ የሰራተኞች ድልድል ከተጠናቀቀ በኋላ BSC ወደ ተግባር እንደሚገባ፣ ለሰራተኞች ልዩ ልዩ የአቅም ማጎልበቻ ስልጠናዎች መሰጠታቸውን፣ የመረጃ ማደራጀት፣ የስታንዳርድ ዝግጅት እና የሕፃናት ማቆያ በመሰራት ላይ እንደሚገኝ የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ አልመው መንግስትና ሌሎች የስራ ሃላፊዎች በዋናነት አብራርተዋል፡፡

በሌላ በኩል ኤጀንሲው አብሯቸው ከሚሰሩ ተቋማት ጋር ተቀናጅቶና ተናቦ በመስራት፣ በፍቃድ አሰጣጥ፣ በወሰን ማስከበርና በካሳ ክፍያ፣ በግዥ መጓተት ረገድ እንዲሁም በአንዳንድ ተቋማት በኩል ኤጀንሲው በአዋጅ የተሰጠውን ስልጣንና ሃላፊነት አለመቀበል አዝማሚዎች መታየታቸውን ሀላፊዎች በእጥረት አንስተዋል፡፡

የቋሚ ኮሚቴ አባላት የተለያዩ የስራ ክፍሎችን እንቅስቃሴ ተዟዙረው ከጎበኙ በኋላ ሰራተኞችን ባወያዩበት ወቅት አንዳንድ ከፍሎች ተገቢውን አቅም ማጎልበቻ ስልጠና እንደማያገኙ፣ የግዥ መጓተት፣ የበጀት፣ የደመወዝና ጥቅማ ጥቅም እንዲሁም የመስክ ተሽከርከሪ እጥረት መኖሩን ሰራተኞቱ በውስንነት ካነሷቸው መካከል ይገኙበታል፡፡

የቋሚ ኮሚቴው ቡድን መሪ የተከበሩ አቶ ዶጊሶ ዶና በሰጡት ግብረ መልስ ኤጀንሲው የመልካም አስተዳደርና የኪራይ ሰብሳቢነት ማክሚያ ዕቅድ አዘጋጅቶ ወደ ስራ መግባቱን፣ በ55 ፕሮጀክቶች ላይ ተገቢው ክትትል መደረጉን፣ ለሰራተኞችና ለባለድርሻ አካላት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መሰጠቱን፣ የመረጃ ማሰባሰብ፣ የንብረት ቆጠራ መደረጉን፣ ስቶክና ቢን ካርድ በአግባቡ በስራ ላይ መዋላቸውንና ሙሉ በሙሉ ባይጠናቀቅም የህፃናት ማቆያ ስፍራ መዘጋጀቱን ቋሚ ኮሚቴው በምልከታው በጥንካሬ ያያቸው አፈፃጸሞች መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡

በሌላ በኩል የለውጥ ስራዎች ጅምር እንጂ ሙሉ በሙሉ ወደ ሥራ ያለመግባታቸውንና ወጥ ሆነ አስተሳሰብ ያለመፈጠሩን፣ ኤጀንሲው በአዋጅ የተሰጠውን ስልጣንና ተግባር በአግባቡ እየተወጣ አለመሆኑንና ከሚመለከታቸው አካላት ጋርም ያለው ቅንጅታዊ አሰራር ደካማ መሆኑን በእጥረት አስቀምጠዋል፡፡

በቀጣም ኤጀንሲው በአዋጅ የተሰጠውን ስልጣንና ተግባር አዋጁ እስካልተሻረ ድረስ መተግበር እንዳለበትና በዚህም ረገድ ለሚመለከታቸው አካላት በቂ ግንዛብ በመፍጠር አብሯቸው ከሚሰሩ ተቋማት ጋር ያለውን ቅንጅታዊ አሰራር ማጠናከር እንዳለበት አሳስበዋል፡፡

የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ አልመው መንግስት በቋሚ ኮሜቴውና በሰራተኞቹ የቀረቡት አስተያየቶች ተገቢነት ላቸው መሆኑን ገልፀው፣ ስልጠና ግን በተቻለ መጠን ለሁሉም ሰራተኛ እንደሙያው እየተሰጠ መሆኑን ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

ኤጀንሲው አብሮ ከሚሰራቸው አካላት ጋር ስላለው ቅንጅታዊ አሰራርና ስልጣንና ተግባሩን በአግባቡ እንዲወጣ በማድረጉ ረገድ የቋሚ ኮሚቴውና የም/ቤቱ እገዛ እንደሚያስፈልግም ነው ሃላፊው የጠየቁት፡፡