null Government Allocates 500 Million Birr

የሶስቱን አዋጆች መጽደቅ አስፈላጊነት በተመለከተ የውሳኔ ሃሳብና ሪፖርት ያቀረቡት  የህግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ጴጥሮስ ወልደ ሰንበት በአዋጆቹ ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር ሰፊ ውይይት እንደተደረገባቸው ለምክር ቤቱ አብራርተዋል፡፡

የፀደቁት ረቂቅ አዋጆች የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁጥር 213/1992ን እንደገና ለማሻሻል፣ የፍትህ፣ የህግ ምርምርና ስልጠና ኢንስቲትዩት ለማቋቋም እንዲሁም የፌደራል ኤሌክትሮኒክ ፊርማ ለመደንገግ የቀረቡ ሲሆኑ፤ ም/ቤቱ ረቂቅ አዋጆቹን አስመልከቶ የቀረቡትን ሪፖርቶችና የውሳኔ ሃሳቦችን መርምሮ የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁጥር 213/1992ን በሶስት ድምጸ ተአቅቦ፣ በሶስት ተቃውሞ በአብላጫ ድምጽ አፅድቆታል፡፡

በሌላ በኩል ም/ቤቱ የፍትህ፣ የህግ ምርምርና ስልጠና ኢንስቲትዩትን ለማቋቋም እና የፌዴራል ኤሌክትሮኒክ ፊርማ ለመደንገግ የቀረቡትን ረቂቅ አዋጆችን ደግሞ በሙሉ ድምጽ አፅድቋቸዋል፡፡