null HE Ato Gedu Andargachew, a former president of the Amhara Regional state, has uttered an Oath as a Minister of Foreign Affairs.

የቀድሞው የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ክቡር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የውጭ ሚኒስትር ሆነው በመሾማቸው ቃላ መሃላ ፈጸሙ፣

የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሚያዝያ 10 ቀን 2011 ዓ.ም.  ባካሄደው 34ኛ መደበኛ ስብሰባው የ3 የሚንስትሮችን ሹመት በአንድ ተቃውሞ በአምስት ድምጸ ተአቅቦ በአብላጫ ድምጽ ማጽደቁ ይታወሳል፡፡

በዕለቱም በጠቅላይ ሚኒስትሩ የታጩትን ተሿሚዎች የመንግስት ረዳት ተጠሪ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ጫላ ለሚ ለም/ቤቱ አቅርበው፤

ክቡር አቶ  ለማ መገርሳ- የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር ሚኒስትር፣

ክቡር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው- የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር እና

ክብርት ኢንጅነር አይሻ መሃመድ- የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ሚኒስትር ሆነው ሹመታቸው በምክር ቤቱ መጽደቁ የምታወስ ነው፡፡

በዕለቱ  ክቡር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በምክር ቤቱ ቀርበው   ቃለ-መሃላ አለመፈጸማቸው የሚታወቅ ሲሆን፣

በምክር ቤቱ የአሰራርና የአባላት ሥነ ምግባር ደንብ የም/ቤቱ ደንብ አንቀጽ 111 መሰረት ዛሬ ሚያዚያ 17 ቀን 2011 ዓ.ም. ከቀኑ 8:30 ላይ በምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ ፊት ቀርበው በጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ክብርት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ አማከኝነት የተጣለባቸውን የህዝብና የመንግስት ሃላፊነት በቅንነት፣ በታተሪነትና ህግና ደንብን መሰረት በማድረግ ለመወጣት ቃለ መሀላ ፈፅመዋል፡፡

የተከበሩ የምክር ቤቱ አፈጉባኤ አቶ ተገሰ ጫፎ ለተሿሚ ሚኒስተሩ  ስከታማ የሥራ ዘመን እንድሆንላቸው መልካም ምኞታቸውን ገልጸውላቸዋል፡፡