null Hon. Deputy Speaker Mrs. Shitaye Minale Meets a Delegation from Sudanese Women Parliamentarian Caucus

የኢትዮዽያ ሴቶች  በፖለቲካ  አመራረ ተሳትፎ፣ የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት እያደገ መምጣቱን ም/አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ሽታዬ ምናለ ለልኡካን  ቡድኑ አባላት  የገለፁ ሲሆን፤ የሴቶች የፓርላማ ተሳትፎም 38 ከመቶ  መድረሱን አስገንዝበዋል፤ የሚያሳየው   በአፍሪካ ደረጃ ሲታይ  የተሻለ  እንደሚባል ነው የጠቆሙት።

የልኡካን ቡድን መሪ ዶክተር ዋፋ ማኪ አህመድ አሊ በበኩላቸው ፤ በሱዳን ፓርላማ  የሴቶች ተሳትፎ  30 ከመቶ መድረሱን እንስተው ፤የፖለቲካ አመራር ብቃታቸውን  ለማሳደግ  ከኢትዮዽያ የፓርላማ ሴቶች ተመራጭ ኮከስ ጋር በቅርበት መስራት  ፍላጎታቸው እንደሆነ ነው የተቆሙት።  

የሁለቱን አገራት የእርስበርስ ግኑኝነት በማጠናከር በአከባቢው አስተማማኝ ሰላም እንዲረጋገጥ እና ለሁለቱ አገራት የጋራ ብልፅግና የሁለቱ ምክር ቤቶች የሴቶች  ኮከስ  የበኩሉን ሚና መጫወት እንዳለባች ግንዛቤ ተይዟል።

የልኡካን ቡድኑ አባላት በታለቁ ህዳሴ ግድብ  ግንባታ  ላይ  ያላቸውን አድናቆት ገልፀው፤ በስፍራው ተገኝተው የግድቡን ግንበታ ለመጎብኘት ፍላጎት እንዳላቸው ገልፀዋል፤ ግድቡ  የሁለቱን አገራት የኢኮኖሚ ትስስር ወደ ተሻለ ደረጃ እንደሚያሸጋግረው የተከበሩ ምክትል አፈ ጉባኤ  ወ/ሮ ሽታዬ ምናለ ለልኡካን ቡድኑ አባላት ገልፀውላቸዋል።