null House passed various bills.

 ምክር ቤቱ  የተለያዩ አዋጆችን አጸደቀ፡፡

መጋቢት 24 /2011 ዓም፤ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው 31ኛ መደበኛ ስብሰባው ለረቂቁ  የተዘጋጀውን   ሪፖረትና የውሳኔ ሃሳብ አድምጦ ስምንት የተለያዩ አዋጆችን መርምሮ አጽድቋል፡፡

ምክር ቤቱ በኢፌዴሪ  መንግስትና በህንድ ሪፐብሊክ መንግስት መካከል በኮሚኒኬሽን ኢንፎርሜሽንና በሚዲያ ዘርፍ የተፈረመውን የትብብር ስምምነት ረቀቅ አዋጅ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል፡፡

የትብብር ስምምነቱ በሁለቱ ሃገራት መካከል ያለውን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የሚያጠናክርና የጋራ ተጠቃሚነትን የሚያጎለብት እንደሆነ የውጭ ግንኙነትና ሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ተስፋዬ ዳባ ገልጸዋል፡፡

 በተመሳሳይ ምክር ቤቱ በኢፌዲሪ መንግስትና በኮትዲቮር ሪፐብሊክ መንግስት መካከል የዲፕሎማቲክ እና ሰርቪስ ፓስፖርት ለያዙ ሰዎች ቪዛን ለማስቀረት የተፈረመውን የትብብር ስምምነት ለማጽደቅ የቀረበ ረቂቅ አዋጅን በሙሉ ድምጽ አጽድቆታል፡፡

ስምምነቱ ሃገራችን የልዩ ልዩ አህጉራዊና አለማቀፋዊ ተቋማት መቀመጫ በመሆኗ ከኮቲዲቮር ወደ ሃገራችን የሚመጡ ዲፕሎማቲክና ሰርቪስ ፓስ ፖርት የያዙትን ዲፕሎማቶችና ሰራተኞች ፍላጎት የሚያነሳሳ እና የሃገራችን የገጽታ ግንባታ የሚያሳድግ መሆኑን አቶ ተስፋዬ ተናግረዋል፡፡

ምክር ቤቱ በኢፌዲሪ መንግስትና በቬንዙዌላ ቦሊቫሪያ ሪፐብሊክ መንግስት መካከል የተደረገውን የባህል ዘርፍ ትብብር  ስምምነት ለማጽደቅ የቀረበለ ረቂቅ አዋጅ  በሙሉ ድምጽ አጽድቋል፡፡

ሃገራችን ቀደምት ባህላዊና እውቅ የባህል ቅርሶች ባለቤት ከመሆኗ አንጻር ስምምነቱ ፋይዳው ዘርፈ ብዙ መሆኑን አቶ ተስፋዬ ጠቅሰዋል፡፡

እንዲሁም ምክር ቤቱ በኢፍዲሪ መንግስትና በጋና ሪፐብሊክ መንግስት መካከል በኮሚኑኬሽን እና በሚዲያ ዘርፍ የተፈረመውን የትብብር ስምምነት ለማጽደቅ የቀረበ ረቂቅ አዋጅን በተመለከተ የቀረበለትን  ረቂቅ አዋጅ  በሙሉ ድምጽ አጽድቋል፡፡

ስምምነቱ ሁለቱ ሃገራት ኮሚዩኒኬሽን ፣ ኢንፎርሜሽንና ሚዲያ ዘርፍን በማዳበር የጋራ ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚያስችልና የወንድማማችነት ግንኙነታችን የበለጠ ተጠናክሮ እንዲቀጥል የሚረዳ መሆኑን አቶ ተስፋዬ አብራርተዋል፡፡

 በመቀጠልም ምክር ቤቱ የኦዝን ንጣፍን የሚያሳሱ ኬሚካሎችን ለመቆጣጠር በሞኒተሪያል ፕሮቶኮል ላይ የተደረገውን የኪጋሊ ማሻሻያ ስምምነት ያጸደቀ ሲሆን፤ ሃገራችን የኪጋሊ የማሻሻያ ስምምነት ተግባራዊ የተጣለባትን ሃላፊነት ለመወጣት በምታደርገው እንቅስቃሴ ከበለጸጉ ሃገራት የገንዘብ ፣ የቴክኖሎጅና የአቅም ግንባታ ድጋፍ የምታገኝ እንደሆነ በምክር ቤቱ የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ተስፋዬ ዳባ የተናገሩ ሲሆን፤ ምክር ቤቱም ተወያይቶ ረቂቅ አዋጁን በሙሉ ድምጽ አጽድቆታል፡፡

 ምክር ቤቱ  አክሎም በኢፌዴሪ መንግስትና በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች መካከል የተፈረመውን የዴፕሎማቲክ ፓስፖርት ለያዙ ሰዎች ቪዛን ለማስቀረት የትብብር መግባቢያ ሰነድ ረቂቅ አዋጅ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል፡፡

ሰነዱ ወደ ሃገሪቱ  የመንግስት የስራ ሃላፊዎችና ሰራተኞች ቩዛን ለማውጣት  ሲያጠፉት የነበረውን ጊዜ በማስቀረት ስራን የሚያቀላጥፍ ፣ ግንኙነታችን የበለጠ የሚያሻሽል  እንደሆነ የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢው አቶ ተስፋዬ ዳባ አብራርተዋል፡፡

 በተጨማሪም ምክር ቤቱ በኢፌዲሪ መንግስትና በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች መካከል የተፈረመውን የኢንቨስትመንት ማስፋፊያ ጥበቃ ስምምነት ረቂቅ አዋጅ በሙሉ ድምጽ ያጸደቆ ፤የስምምነት ረቂቁ ሃገራችን የተያያዘችውን ወደ ኢንደስትሪ የሚደረግ ሽግግርን የሚያቀላጥፍና የወጪና የገቢ ምርቶች እንዲያድጉ የሚያግዝ ስምምነት እንደሆነ የውጭ ግንኙነትና ሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ተስፋዬ ደባ ጠቅሰዋል፡፡

በመጨረሻም ምክር ቤቱ የጅምላ ጨራሽ መሳሪያዎች ብዜትን በገንዘብ መደገፍን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የቀረበ ረቂቅ አዋጅ በሙሉ ድምጽ አጽድቆታል፡፡

ኢንቨስተሮችና ሃገራት ወደ ሃገራችን ያለምንም ስጋት ገንዘብ ማንቀሳቀስ እንዲችሉ የሚያበረታታ  መሆኑን የውጭ ግንኙነትና ሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ተስፋዬ ዳባ አብራርተዋል፡፡