null House passed various bills.

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተለያዩ አዋጆችን መርምሮ አፅድቋል፡፡

ምክር ቤቱ ጥር 29 ቀን 2011 ዓ.ም ባደረገው ሶስተኛ ልዩ ስብሰባ የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴና የግርና፣ አርብቶ አደር አካባቢ ጥበቃ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በኢ.ፌ.ዲ.ሪ መንግስትና በአልጀሪያ ህዝባዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት መካከል በእጽዋት ማቆያና ጥበቃ ዘርፍ የተደረገውን ስምምነት ለማጽደቅ በቀረበው የውሳኔ ሀሳብ ላይ በዝርዝር ተወያይቷል፡፡ 

ረቂቅ አዋጁ በሁለቱ ሀገራት መካከል በእጽዋት ማቆያና ጥበቃ የተፈረመው የትብብር ስምምነት መረጃም ሆነ ልምድ በመለዋወጥ ሊከሰቱ የሚችሉ የእጽዋት ተባዮችንና በሽታዎችን ለመከላከል፣ ለማከምና ለመቆታጠር የሚያስችል ሲሆን በዘርፉ ያለውን አቅም ለማሳደግ የእውቀትና ቴክኖሎጅ ሽግግር በመፍጠር የሀገራቱን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የበለጠ እንዲጠነክር የሚግዝ በመሆኑ ተብራርቷል፡፡

ም/ቤቱም ረቂቅ አዋጁን መርምሮ አዋጅ ቁጥር 1118/2011 ሁኖ ያለምንም ተቃውሞና ተዓቅቦ በሙሉ ድምጽ አፅድቋል፡፡

የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚቴና የህግ፣ ፍትና ዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በአ.ፌ.ዲ.ሪ መንግስትና በአልጀሪያ ህዝባዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት መካከል በኮሚኒኬሽንና ኢንፎርሜሽን ዘርፍ፣ በዘመናዊ ኢንፎርሚሽን ኮሚኒኬሽንና ሚዲያ ቴክኖሎጂ፣ በቴሌቪዥንና ራዲዮ ስርጭትና ስልጠናና በዘርፉ ልምድና የእውቀት ሽግግር ለመለዋወጥና ተሞክሮ ለማስተላለፍ እንዲሁም ሁለቱ አገራት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የበለጠ የሚያጠናክር እንደሆነ የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ ተስፋዬ ዳባ አስረድተዋል፡፡

ምክር ቤቱ በረቂቅ አዋጁ ላይ ተወያይቶ ረቂቅ አዋጅ 1119/2011 አድርጎ ያለምንም ተቃውሞ አፅድቆታል፡፡

በተጨማሪም የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በኢ.ፌ.ድ.ሪ መንግስትና በኳታር መንግስት መካከል የዲፕሎማቲክ ወይም ልዩ ፓስፖርቶች ለያዙ ሰዎች ቪዛን ለማስቀረት የተፈረመውን ስምምነት ለማጽደቅ በቀረበው ረቂቅ አዋጅ ላይም ም/ቤቱ ተወያይቷል፡፡

ረቂቅ አዋጁ የሁለቱ ሀገራት ዲፕሎማቲክና ሰርቪስ ልዩ ፓስፖርት የያዙ ባለስልጣናት፣ የሀገር መሪዎችና ዜጎች ቪዛ ለማስፈቀድ የሚኖረውን ጊዜ በማሳጠርና የስራ ቅልጥፍናን ለማሳደግ እንደሚያስችል ተብራርቷል፡፡

ምክር ቤቱ ረቂቅ አዋጁ መርምሮ አዋጅ ቁጥር 1120/2011 ሆኖ በሙሉ ድምጽ እንዲፀድቅ ወስኗል፡፡

በተመሳሳይም የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሰው ሀብትና ቴክኖሎጅ ጉዳዮች በኢ.ፌ.ድ.ሪ መንግስትና በኳታር መንግስት መካከል የተፈረመውን የአጠቃላይ ትምህር፣ ከፍተኛ ትምርት ተቋማትና የሳይንስ ምርምር ዘርፍ ትብብር የመግባቢያ ሰነድ ለማጽደቅ የቀረበ የውሳኔ ሀሳብ ላይም መክሯል፡፡

የረቂቅ አዋጁን አስፈላጊነት በሚመለከት በቀረበው ማብራሪያ በኢትዮጵያና በኳታር መካከል የተደረሰው ትምህርት ዘርፍ ትብብር ስምምነት በጋራ በመስራት ልምድ በመለዋወጥ እውቀትና የቴክኖሎጅ ሽግግር በመፍጠር በትምህርት ዘርፉ በየሚታዩ ክፍተቶችን ለመሙላትና የትምህርት ጥራትን ከማገዙም በላይ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን በማጠናከር የሀገራቱን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የሚያጎለብት በመሆኑ ተጠቁሟል፡፡

ከውይይቱ በኋላ ምከር ቤቱ ረቂቅ አዋጁ አዋጅ ቁጥር 1121/2011 ሁኖ በሙሉ ድምጽ አፅድቋል፡፡

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ ማብራሪያ ያቀረቡት የመንግስት ረዳት ተጠሪ ሚኒስቴር ዴኤታ አምባሳደር መስፍን ቸርነት ምርጫ ቦርዱ ጠንካራ፣ ገለልተኛና ከአድሎ ነጻ ሁኖ እንዲሰራና የቦርዱ አባላት ሙሉ ስራቸውን በንቃትና በተቀናጀ መንገድ እንደሚሰሩ የሚስችል መሆኑን አብራርተዋል፡፡

የምክር ቤቱ አባላት በበኩላቸው ረቂቅ አዋጁ ከመመራቱ በፊት ቦርዱ ከዚህ በፊት ይነሱበት የነበሩበትን የብቃት ጥያቄዎች የሚፈታ መሆን እንደሚገባው፣ ገለልተኛ ሰዎች ከየት ከየት መመረጥ እንዳለባቸው ግልጽ ቢደረግ፣ አዋጅ ቁጥር 532/1999ን ሙሉ በሙሉ ማስተካከል የሚቻልበት መንገድ ቢኖርና የሴቶች ተሳትፎ መካተት አለበት የሚሉት አስተያየቶች አንስተዋል፡፡

ቀድሞ በነበረው ምርጫ ቦርድ በተፎካካሪ ፓርቲዎች ብዛት ያላቸው ቅሬታዎች በተለያዩ ሚዲያዎችና መድረኮች ጭምር ይነሱበት ስለነበር የሁሉንም ወገኖች ጥያቄ ሊፈታ የሚችል ገለልተኛና ነጻ የምርጫ ቦርድ መሆን እንዳለበት አሳስበዋል፡፡

የቦርዶች አሰያየም በተመለከተ ከዚህ በፊት ችግር እንደነበር በተደጋጋሚ ይነሳ እንደነበርና ከተጠያቂነትና ነጻ ሁኖ ከመስራት አኳያ ችግር እንደነበረበት የተከበሩ አቶ ተስፋዬ ዳባ በምላሻቸው አስረድተው አሁን የሚመደቡት የቦርድ አባላት በጠቅላይ ሚኒስቴሩ የሚሰራ ሳይሆን ሁሉንም አካል ያሳተፈ ነው ብለዋል፡፡

House passed various bills.