null House told Ministry that the implementation of labor law should not delay by any reason.

የውጭ አገር የስራ ስምሪት ትግበራው በተለያዩ ምክንያቶች  መጓተት እንደሌለበት ተገለጸ

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ31ኛ መደበኛ ስብሰባው የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴርን የ2011 በጀት ዓመት የስምንት ወራት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት አዳምጧል፡፡

የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ በሪፖርታቸው በአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ ዘርፍ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ሰላም እንዲሰፍን፣ የሰራተኞች የስራ ላይ ደህንነትና ጤንነት እንዲጠበቅ፣ እንዲሁም በማህበራዊ ዘርፍ አካል ጉዳተኞች እና አረጋውያን እኩል ተጠቃሚና ተሳታፊ እንዲሆኑ ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በቅንጅት እየሰሩ እንደሆነ አስረድተዋል፡፡

በስራ ቦታ ላይ የህግ ተፈጻሚነትን ለማረጋገጥ በተደረገው ቁጥጥር 4394 ድርጅቶች ህጉን በመተላለፋቸው የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ሲሆን 5 ድርጅቶች ደግሞ በህግ ተጠያቂ ማድረጋቸውን ሚኒስትሯ ተናግረዋል፡፡

በተመሳሳይም ለአሰሪና ሰራተኛ አገናኝ ኤንሲዎች የፍቃድ አሰጣጥና እድሳትን አስመልክቶ በርካታ ስራዎች እንደተሰሩ የገለጹት ሚኒስትሯ ዶክተር ኤርጎጌ በሌላ በኩል በተረገው የክትተልና የቁጥጥር ስራ ህግ በመተላለፋቸው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ብቻ 113 ኤጀንሲዎች ፈቃዳቸው የታገደ ሲሆን የ12ቱ ደግሞ ፈቃዳቸው መሰረዙን ይፋ አድርገዋል፡፡

ሚኒሰስትሯ አክለውም የውጭ አገር የስራ ስምሪትን በተመለከተም ከተለያዩ አረብ አገሮች ጋር የድፕሎማሲ ድርድሮች ቢካሄዱም በርካታ ቀሪ ስራዎች በመኖራቸው በተቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ዜጎችን ወደ ውጭ መላክ አልተቻለም ብለዋል፡፡

ምክር ቤቱ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በሪፖርቱ ላይ የተሰበሰቡ ጥያቄ አሰተያየቶችን በማከል በተቆሙ ላይ የታዩ ክፍተቶችና መሻሻል አለባቸው ያለውን ጉዳዮች በዝርዝር ገምግሟል፡፡ ከተነሱ ጉዳዮች ውስጥ የሰራተኛና ማህበራዊ የሴክተር አደረጃጀት አስከ ታችኛው መዋቅር ተዘርግቶ ለዜጎች ተደራሽ አለመሆኑን፣ በአሰሪና በሰራተኞች መካከል ጤናማ ግንኙነት እንደሌለ፣ አካል ጉዳተኞችን፣አረጋውያንና ለማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ተጋላጭ የሆኑትን የህብረተሰብ ክፍሎች አካቶ ከመስራት አንጻር ክፍተቶች እንዳሉ ማመላከት ተችሏል ፡፡

በተጨማሪም በአሰሪና ሰራተኛ መካከል የሚከሰቱ አለመግባባቶችን ለመቅረፍ፣ ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመግታት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንዳለበት ጠቁሞ  ለአረጋውያን፣ ለአካል ጉዳተኞንና ለጎዳና ተዳዳሪዎች ሁለንተናዊ ድጋፍ ሊደረግ እንደሚገባ አሳስቧል፡፡

የውጭ አገር የስራ ስምሪትን በተመለከተም አዋጁ ከወጣ በኋላ ወደ ተግባር ተገብቶ ዜጎች ወደ ውጭ አገር እየተላኩ አይደለም፣ አሰራሩ የተጓተተ በመሆኑ ዜጎች ሳይፈልጉ ለህ-ገወጥ ስደት እየተዳረጉ ነው ሲሉ የምክር ቤቱ አባላት ተናግረዋል፡፡

የሴቶች ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ ወ/ሮ አበባ ዮሴፍ በበኩላቸው የተቋሙ እቅድ አሳታፊ በሆነ መንገድ ታቅዶ አስከታችኛው መዋቅር መውረዱን፣በተለያዩ ምክንያቶች ለኢኮኖሚ ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን በዘላቂነት ለማቋቋም የተደረገውን ጥረት፣እንዲሁም የማህበራዊ ዋስትና ሽፋንን ለማሳደግ በግል ተቋማት ተቀጥረው የሚሰሩ ዜጎች የጡረታ ተጠቃሚ እንዲሆኑ መደረጉን በጥንካሬነት ገልጸዋል፡፡

በሌላ በኩል በአሰሪና ሰራተኞች መካከል የሚታዩ አለመግባባቶች ሰርአት ተበጅቶለት ክትትል የሚደረግበት አግባብ የማጠናከር ፣ የሙያ ደህንነት ጥበቃ ተጠናክሮ የሚቀጥልበት ፣ እንዲሁም አካል ጉዳተኞን አረጋውያንና የጎዳና ተዳዳሪዎችን በዘላቂነት የማቋቋም ስራዎች የበለጠ ትኩረት የሚሹና ትኩረት ተሰጥቶ ሊሰራባቸው የሚገቡ  ጉዳዮች መሆናቸውን አመላክተዋል፡፡