null Legal, Justice and Democracy Affair Standing Committee discussed with stakeholders regarding the establishing a draft proclamation of Ombudsman.

የህግ፣ ፍትህና ዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ  የህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ማቋቋሚያ አዋጅን ለማሻሻል በወጣው ረቂቅ አዋጅ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር  ውይይት አካሄደ

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የህግ፣ ፍትህና ዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ዛሬ ታህሳስ 22 ቀን 2011 ዓ.ም  ባካሄደው ስብሰባው የህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ማቋቋሚያ አዋጅን ለማሻሻል በወጣው  ረቂቅ አዋጅ ላይ ከተለይዩ ተቋማት ከመጡ ባለድረሻ አካላት ጋር ውይይት  አካሄዷል፡፡

በምክር ቤቱ የማሻሻያ አዋጅ  መወጣት አስፈጊነት ዙሪያ የህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ዋና እንባ ተባቂ የሆኑት ደ/ር እንዳለ  ኃይሌ  እንደገለፁት አዋጁ  አለም አቀፍ ህጎችን  መሠረት በማድረግ እንዲሻሻል ከመደረጉም ባለፈ ከተቋሙ ዓለማቀፋዊ ባህሪያት መካተት ያለባቸው  አንቀጾችን ለማካተት ታስቦ  የቀረበ  የማሻሻያ አዋጅ መሆኑን ጠቁመው በነባሩ አዋጅ ውስጥ ተካተው ግን  ለአፈጻጸም አስቸጋሪ የሆኑ ድንጋጌዎች፣ ግልፅነት የጎደላቸውና እርስበርሳቸው የሚጋጩ እንዲሁም አሻሚ የሆኑ  ሃሳቦችን  የያዙ አንቀፆች መኖራቸውን  በማንሳት የአዋጁን መሻሻል አስፈላጊ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ሌላው ነባሩ  አዋጅ በአስፈጻሚ አካላት የሚሰጠው የመፍትሄ  ሃሳብ ሳይፈፀሙ ኃላፊነታቸውን የሚወጡ  አካላት መብትና ግዴታን በግልጽ አያስቀምጥም አዲሱ አዋጅ ግን በተሻለ መንገድ ኃላፊነታቸውና ግዴታቸው ምን እንደሆነና ግዴታቸውን ባይወጡ የሚወሰደው እርምጃም ጭምር በግልጽ ያካተተ መሆኑ፣ አስተዳደራዊ በደሎችን ይፈፀማሉ ተብለው የተቀመጠው በክልሎች ብቻ  የነበረ ሲሆን በአዲሱ አዋጅ ግን  በክልልሎችና በፌዴራል ተቋማት ላይ የሚፈፀሙ አስተዳደራዊ በደሎች በሚል የተሰተካከለበት ሁኔታ ነው ያለው የሚሉና ሌሎችንም ለአዋጁ መሻሻል አስፈላጊናቸው ያሉትን ሃሳቦች በማንሳት በዝርዝር አስረድተዋል፡፡

የቀረበውን የመሻሻያ አዋጅ አስፈላጊነት  መነሻ በማድረግ ከተሳታፊዎቹ የተለይዩ ጥያቄዎችን ቢካተቱ የማሻሻያ አዋጁን ሙሉ ያደርጉታል ተብለው ለተነሱ በርካታ አስተያየቶች  ከህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም የመጡ የስራ ኃላፊዎች ማብራሪያ ሰተውባቸዋል፡፡

በመጨረሻም በቋሚ ኮሚቴው የዲሞክራሲ ጉዳዮች ንኡስ ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት ወ/ሮ የሺመቤት ነጋሽ በበኩላቸው የተነሱ ሃሳቦች  ተገቢነት ያላቸው ከመሆኑም ባለፈ ቋሚ ኮሚቴው ለሚያዘጋጀው የውሳኔ ሃሳቡ  ጥሩ ግብአት የሚሆኑ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

 ተቋሙ በመድረኩ የተነሱትን ሃሳቦች በማካተት በአጭር ጊዜ ውስጥ ለቋሚ ኮሚቴው መላክ እንዳለበት አሳስበዋል፡፡