null Members of the Uk parliament delegation said they will continue strengthening the all round relations between Ethiopia and Uk.

በኢትዮጵያና ዩናይትድ ኪንግደም መካከል ያለውን ሁለንተናዊ ግንኙነት አጠናክረው እንደሚቀጥሉ የዩናይትድ ኪንግደም ፓርላሜንታዊ  ልዑካን ቡድን ገለጸ፡፡

በህዝብ  ተወካዮች  ምክር   ቤት  የውጭ  ግንኙነትና ሰላም ጉዳዮች  ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ  አቶ ተስፋዬ ዳባ  የተለያዩ  የፖለቲካ ፓርቲዎችን ያካተተውን  የዩናይትድ  ኪንግደም  ፓርላሜንታዊ  ልዑክ  በጽ/ቤታቸው  ተቀብለው  አነጋግረዋል፡፡

የልዑካን  ቡድኑ  የሁለቱን  ሃገራት  ግንኙነት  ለማጠናከርና  በፓርላማዎቹ  መካከል  የሃሳብ  ለውውጥ ለማድረግ  እንደሆነ   ገልጿል፡፡

 የኢትዮጵያ  መንግስት  የፖለቲካ ስነ-ምህዳሩን  ለማስፋት በአጭር  ጊዜ  ውስጥ   ያከናዎናቸውን  ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር  ቡድኑ  አድንቋል፡፡

የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ  ተስፋዬ  ዳባ በበኩላቸው  የኢትዮጵያና  ዩናይትድ ኪንግድም  ግንኙነት እ.ኤ.አ.  ከ 1897 ዓ.ም ጀምሮ የተመሰረተ መሆኑን አውስተው፤  በባህል፣ በስነ-ምጣኔና  በፖለቲካ ጉዳዮች ዙሪያ በትብብር እየሰሩ እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡

ሀገሪቱ  ሽብርተኝነትን  ለመከላከልና  የሰላም ማስጠበቅ ተልዕኮን  ለማረጋገጥ  ከኢትዮጵያ ጋር እየሰራች እንደምትገኝ  የጠቀሱት አቶ ተስፋዬ ፤ በደቡብ ሱዳን ተፈጥሮ  የቆየውን  የፖለቲካ  አለመግባባት ለመፍታት  ሁለቱ  ሃገራት  በትብብር  ሲሰሩ እንደነበር   ለልዑካን  ቡድኑ  አብራርተውላቸዋል፡፡

የፖለቲካ  ለውጡን  ተከትሎ  ለውጡን  ያልተቀበሉ  ሃይሎች  በሚፈጥሩት  ችግር  የዜጎች መፈናቀል እየገጠመ  እንደሆነ  ያብራሩት  አቶ ተስፋዬ፤ ችግሩን  ለመፍታት  መንግስት  በተቋም ደርጃ ተግቶ እየተንቀሳቀሰ  እንደሚገኝ  ተናግረዋል፡፡

የሁለቱን  ሃገራት  የፓርላማ  ግንኙነት  አጠናክሮ ለ ማስቀጠል  ዩናይትድ  ኪንግደም  በአቅም ግንባታ በኩል  ድጋፍ  እንድታደረግ  የልዑካን ቡድኑን ጠይቀዋል፡፡

በመጨረሻም የልዑካን ቡድኑ “ ጉዞ ሉሲ ለሰላምና ለፍቅር“ በሚል መሪ ቃል  የተዘጋጄው  አውደ ርዕይ ላይ ተገኝተው  ገለጻ  ተደርጎላቸዋል፡፡