null Over the past forty-five years, there has been a significant loss of civilian population in Ethiopia.

በኢትዮጵያ ውስጥ በእርስ በርስ ግጭት ባለፉት አርባ አምስት አመታት በጣም ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰው ማጣቷ ተጠቆመ፡፡

በኢትዮጵያ ውስጥ በእርስ በርስ ግጭት ባለፉት አርባ አምስት አመታት በጣም ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰው ማጣቷንና ብዙ ሰዎች ለአካል ጉዳት የተዳረጉ መሆኑን በማስታወስ ከባለፈው ታሪክ መማር እንደሚገባ ተጠቆመ፡፡

የኢፈዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ አመት የስራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ስብሰባውን ዛሬ ጥቅምት 11 ቀን 2012 ዓ.ም አካሂዷል፡፡

የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ክብርት ወ/ሮ ሳህለ ወርቅ ዘውዴ መስከረም 26 ቀን 2012 ዓ.ም ለህዝብ ተወካዮችና ለፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ ስብሰባ የመክፈቻ ንግግር ማድረጋቸው ይታወሳል፤ ዛሬ ደግሞ ንግግሩን አስመልክቶ ከምክር ቤቱ ለቀረቡ ጥያቄዎች የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስተር ዶ/ር አብይ አህመድ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

ከምክር ቤቱ የተለያዩ ጥያቄዎች ተነስተዋል፡፡ ከወሎ ህዝብ ጋር ተያይዞ ለተነሳው  ጥያቄ  ፕሮግራም አመቻችተው የሚያናግሩዋቸው መሆኑ ገለጸው፤ በክልሎች መካከል የቃላት ጦርነትና ፉክክር አለ ለሚለው ትልቁ ችግር ካለፈው ታሪክ ስህተት ተምሮ አለማረምና የባለፈን ወረት አለመጠቀም ችግር መሆኑን አንስተዋል፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ በእርስ በርስ ግጭት ባለፉት አርባ አምስት አመታት በጣም ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰው ማጣቷንና ብዙ ሰዎች ለአካል ጉዳት የተዳረጉ መሆኑን አስታውሰው  ያለፈውን ስህተትና ኪሳራ መዘንጋትና አለመቀበል ካለ ግን ችግሩ መልሶ ሊያጋጥም እንደሚችል አሳስበዋል፡፡

ችግር በውጊያ እንደማይፈታና በየጊዜው ግጭት እየቀሰቀሱ መኖር የሚፈልጉ ሰዎች ስላሉ ወጣቱ መንቃት እንዳለበትም አሳስበዋል፡፡ ችግሩን በፈጠረው አስተሳሰብ ችግሩን መፍታት እንደማይቻልና ችግሩን የፈጠረውም በክላሽ መፍትሄ አመጣለሁ ማለት መሆኑን አንስተው ይህን አስተሳሰብ ለመቀየር ህዝቡም ጥረት ማድረግ እንዳለበት ገልጸዋል፡፡  

የውስጥ ሰላም ጉዳይን በሚመለከት እስካሁን በተሰሩ ስራዎች የተፈናቀሉ ዜጎች እንዲመለሱ መደረጉንና የታሰሩ ሰዎች መፈታታቸውን ጠቁመዋል፡፡

የአካል ጉዳተኞችን በሚመለከት አነሱን ታሳቢ ያደረገ ዕቅድ በማውጣት መስራት እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡

የኑሮ ውድነትን በሚመለከትም የቤት ችግር ለመፍታት መንግስት ሰፊ ዕቅድ ይዞ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን፣ የጎዳና ተዳዳሪዎችን በማንሳት ስራ መስጠትና ዳቦ እንዲያገኙ ማድረግ፣ ምግብን በሚመለከት በቀን ከአንድ ሚሊየን በላይ ዳቦ ማምረት የሚችል ፋብሪካ በመሰራት ላይ መሆኑንና በቅርቡ የሚያልቅ በቀን አስር ሺ ዳቦ የሚያመርት ፋብሪካ እየተሰራ እንደሆነ እንዲሁም የከተማ እርሻን በማስተዋወቅ የዋጋ ንረትን ለመቀነስና የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋት ጥረት እንደሚደረግ አንስተዋል፡፡