null Space science steps prosperity of the nation: House Speaker

ሀገራችን የስፔስ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ መሆንዋ ለልማት ስራችን አጋዥ መሆኑን አፈ ጉባኤ፣

ሀገራችን የስፔስ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ መሆንዋ ለልማት ስራችን አጋዥ መረጃ ከማግኘት ረገድ የብልጽግናችን ማሳያ እና ተስፋ የሚሰጥ ነው ሲሉ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጬፎ ጠቁመዋል፡፡

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤን ጨምሮ የምክር ቤቱ አባላት ዛሬ የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩትን ጎብኝተዋል፡፡

ኢንስቲትዩቱን አስመልክቶ የኢኖቬሽን ቴክኖሎጂ ሚንስተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ ባስተላለፉት መልእክት የኢትዮጵ ስፔስ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በ2009 አ/ም በ32 ዩኒቨርስቲዎች የተቋቋመ መሆኑን ገልጸው ጥራት ያለው እና አለም አቀፍ ተወዳዳሪ የሆነ ምርምር በማድረግ በመስኩ የፈጠራ እና የማህበራዊ አገልግሎት ለህዝባችን ከማቅረብ እና የኑሮ ሁኔታን ከማሻሻል ረገድ ለሃገራዊ ኢኮኖሚ ትልቅ ሚና ያለው ነው ሲሉ አስረድተዋል፡፡

የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤም በጉብኝቱ ወቅት በሰጡን ማብራሪያ ሃገራችን የስፔስ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ መሆንዋ የልማት ስራችንን በየትኛው መንገድ መምራት እንዳለብን አጋዥ መረጃ የሚሰጠን በመሆኑ ሀገራችን በቴክኖሎጂው ተወዳዳሪ እንድትሆን የሚያስችሏት ሙህራንን በማበረታታት ጥላቻን በማስወገድ ከልዩነት ይልቅ አብሮነታችንን ማጎልበት እንደሚገባ ገልጸው የምክር ቤቱም ድጋፍ እንደማይለያቸው አስገንዝበዋል፡፡ አያይዘውም ከዚህ ቀደም ከሌሎች ሃገሮች መረጃን ገዝተን የምንጠቀም መሆናችንን አስታውሰው ይህን ማስቀረታችን ለሃገር እድገት ትልቅ ሚና አለው ሲሉም ጠቁመዋል፡፡

ዘጋቢ:- ለምለም ብዙነህ