null Speaker of the House discussed with Ambassador of Azerbaijan.

ኢ.ፈ.ዴ.ሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ ታገሰ ጫፎ የአዘርባጃን አምባሳደር ኤልማን አብዱላይቭን ተቀብለው አነጋገሩ፡፡

አዘርባጃን ከሶቪየት ህብረት ጋር ከነበረችበት ጊዜ አንስቶ ከኢትዮጵያ ጋር መልካም ወዳጅነት እንደነበራትና ይህንንም በይበልጥ ለማጠናከር እንዲሁም የሁለትዮሽ ፓርላማ ግንኙነትን አንድ ደረጃ ክፍ የሚያደርግ ምክክር እንደሆነ በውይይታቸውም ገልጸዋል፡፡

የተከበሩ አፈ-ጉባዔ አቶ ታገሰ ጫፎ አዘርባጃን ባላት ከፍተኛ ልምድ በቱሪዝም፣ በባቡር መንገድ ዝርጋታ፣ የተፈጥሮ ዘይትና ማዕድናትን በማውጣትና በግንባታው ዘርፍ ኢትዮጵያ በጋራ ለመስራት ፍላጎት እንዳላት ጠቁመዋል፡፡

አምባሳደር ኤልማን አብዱላይቭን   በበኩላቸው እ.እ.አ በ2014 አዘርባጃን ኢምባሲዋን በአዲስ አበባ መክፈቷ ያላትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነትን ከፍ ለማድረግና በኢኮኖሚው ረገድ ድርሻው የጎላ እንደሚሆን አመልክተዋል፡፡  

አምባሳደሩም አክለው በትምህርት ዘርፍ አጫጫጭርና ረጅም ስልጠናዎችን እንዲሁም ነጻ የትምህርት ዕድል እንደሚትሰጥም ነው የተናገሩት፡፡

በመጨረሻም አፈ-ጉባዔ አቶ ታገሰ ጫፎ አዘርባጃን ከሶቪየት ህብረት ጋር በነበረችበት ወቅት ከ500 በላይ ኢትዮጵያውያን የትምርት ዕድል መስጠቷን አስታውሰው፣ በተደረገው ውይይትም በቀጣይም ኢትዮጵያ በምታደርገው የልማት ጉዞ አዘርባጃን በተፈጥሮ ዘይትና በማዕድን ማውጣት እንዲሁም በባቡር ዝርጋታ ያላትን ከፍተኛ ልምድ በማካፈል ድጋፏን እንደምታደርግ ጠቁመዋል፡፡