null Standing committee of the House urged University of Jima to focus on educational qualities

የጅማ  ዩኒቨርስቲ  ትምህርት ጥራትን  ለማስጠበቅ   በትኩረት  እንዲሰራ  በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቴክኖሎጅና የሰው ሀብት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ኣሳሰበ፡፡

ቋሚ ኮሚቴው ወደ ጅማ ዩኒቨርስቲ በማቅናት የመስክ  ምልከታ አድርጓል፡፡ ቋሚ ኮሚቴው ከዩኒቨርስቲው ማህበረሰብ ጋር የተወያየ ሲሆን፤ በዩኒቨርስተዊ  የትምህርት ጥራት እያሽቆለቆለ መምጣቱ ኣሳሳቢ   ነው ተብሏል፡፡

ለትምህርት ጥራ ማሽቆልቆል  ዋና ምክንያትም   የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር ችግር ያለባቸውን መምህራን በተገቢዉ አግባብ አለመከታታሉና አለመቆጣጠር  ነው ተብሏል፡፡

ዴሞክራሲያዊ ግንኙነት በተማሪና መምህራን መካከል   አለመኖሩ፣ የፆታ ትንኮሳዎች መጨመራቸው  እና አንዳንድ መምህራን ተገቢ ባልሆነ መንገድ የተማሪ ውጤት እየሰጡ መሆናቸውን  ቋሚ ኮሚቴው ከተማሪዎች ጋር ባደረገው ውይይት  መታዘብ ችሏል፡፡

የተማሪዎች የምክር አገልግሎት አሰጣጥ ፣ ለሴት ተማሪዎችና አካል ጉዳተኞች የሚደረግ ድጋፍ እና የአካዳሚክ ብቃት ማነስ የሚታይባቸዉን ተማሪዎች ለይቶ የማብቃቱ  ስራ በቂ አለመሆኑ ተጠቅሷል፡፡

በዩኒቨርስቲው  ስር ባሉ አንዳንድ ኮሌጆች የቤተ መጽሀፍት ክፍሎች ከተማሪዎች ቁጥር ጋር አለመመጣጠኑ፤  በቂ የመፃህፍት አቅርቦት አለመኖሩ እና  አንዳንድ መፃህፍት ለአብነት   እንደ የ'Afan oromo' ያሉ ባለመሟላታቸው ሳብያ  ተማሪዎችና መምህራን  መቸገራቸዉ  ተገልጧል፡፡ ቤተ ሙከራዎች በሰዉ ሀይልና በግብዓት ከማሟላት አንጻርም ከተማሪዉ ቁጥር ጋር የማይጣጣም  እና በቤተ ሙከራ ማእከል የጥገና አገልግሎት  ችግር እንዳለም ነው  ቋሚ ኮሚቴው በመስክ ምልከታው መገንዘበ የቻለው፤ ችግቹን ፈጥኖ ለመፍታት ትኩረት እንዲሰጥበት  ቋሚ ኮሚቴው አሳስበዋል፡፡  

የፈተና ድግግሞሽ ከመኖሩም በላይ ተማሪዎች  ከተማሩት  ሞጁሎች ውጭ ፈተና እንደሚፈተኑ እንዲሁም የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ ተማሪን ከማብቃት ይልቅ ማባረርን እንደ መፍትሄ እየተወሰደ መሆኑ እና የህይወት ክህሎት እና  የመሪነት ሥልጠናዎች በተገቢው መንገድ እየተሰጡ ባለመሆናቸው  በአፋጣኝ መስተካል አለበት ሲል ቋሚ ኮሚቴው  በሰጠው ግብረ መልስ አመላክቷል ፡፡

የዩኒቨርሲቲዉ ማህበረሰብ ሰላማዊ የመማር ማስተማር ስራን በዉጤታማነት ለማስኬድ በቅንጅት መስራቱ፣  ዩኒቨርሲቲዉ የአካባቢዉን ማህበረሰብ በጥናትና ምርምር፣ በእንሰሳት ሃብትና በግብርና ስራ መደገፉን እንዲሁም የአንደኛና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን በመማሪያ ቁሳቁስ እና በመማር ማስተማር ለመደገፍ የተደረገውን  ጥረት   ቋሚ ኮሚቴው በተሻለ  አፈፃፀም ገምግሟል፡፡

በተጨማሪም  ተማሪዎች ወደ ማህበረሰቡ በመዉረድ የተለያዩ የማህበረሰብ አገልግሎቶችን እየሰጡ መሆናቸዉ፣ በሲቪል ምህንድስና ዘርፍ የተለያዩ የግንባታ ቁሳቁሶችን በዝቅተኛ ዋጋ  የጥራት ማረጋገጫ ስራዎች መሰራታቸዉ ቋሚ ኮሚቴው በጥሩ ጎኑ አንስቷል፡፡

በዩኒቨርሲቲዉ ማህበረሰብ በመልካም አስተዳደር ዙሪያ የሚነሱ ቅሬታዎችን ለመፍታት  ጥረት እየተደረገ ሲሆን፤የመዝናኛና የምግብ አገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል የግብአት አቅርቦት በጥራትና በመጠን በዉሉ መሰረት ተፈጻሚ እንዲሆን ከተለያዩ አካላት የተወጣጡ አበላትን የያዘ ኮሚቴ ተደራጅቶ እየተሰራ እንደሆነና ለቀጣይም ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ኮሚቴው  አስገንዝቧል፡፡

ጅማ ዩኒቨርስቲ በትምህርትም ሆነ በሌሎች ዘርፎች  ከአፍሪካ ዩኒቨርስቲዎች ቀዳሚ  ለማድረግ አምስት  የጸጥታ ግብረ -ሀይል አቋቁሞ እየሰራ ቢሆንም በግቢው ውስጥ አስቸጋሪ የሆነ የብሄር ተኮር እንቅስቃሴ ከዓመት ዓመት እጨረ መምጣቱነ የውጭ ግንኙነት ሲኒየር ዳይሬክተር የሆኑት ደ/ር አሸናፊ በላይ ቋሚ ኮሚቴው አባላት ገልጸውላቸዋል፡፡

መንግስት ወደ ዩኒቨርስቲ የሚገቡትን ተማሪዎች ከየትኛው ፖለቲካ ነጻ ሁነው እንዲገቡ ልዩ ትኩረት አድርጎ ካልሰራ በዩኒቨርስቲው ማህበረሰብም ሆነ እንደ አገር  ችግር  ሊፈጥር እንደሚችል ያለውን ስጋት ዶ/ር አሸናፊ በላይ  አክለው ለቋሚ ኮሚቴው አባላት አንስተዋል፡፡