null Standing committee of the House visited Tirunesh begging general Hospital.

በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሴቶች፣ ወጣቶች እና ማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በጥሩነሽ ቤጂንግ አጠቃላይ ሆስፒታል ጉብኝት አደረገ፡፡

ቋሚ ኮሚቴው ሆስፒታሉ ባጋጠመው የቦታ ጥበት እና የህክምና መሳሪያዎች እጥረት ምክንያት  መዳረጉን ተመልክቷል፡፡

ተቋሙ ለሕብረተሰቡ አገልግሎት ለመስጠት ጥረት እያደረገ ቢሆንም በሆስፒታሉ ተከዝነው የተቀመጡ የሕክምና መሳሪያዎች በክፍል ጥበት ምክንያት አገልግሎት እየሰጡ ባለመሆናቸው ህክምናውን ፈልገው የሚመጡ ታካሚዎች አገልግሎቱን ሳያገኙ የሚመለሱበት አጋጣሚ እንዳለም ማወቅ ተችሏል፡፡ ከዚህ ጋር ተያየይዞም ባለው የሕክምና መሳሪያ እጥረት ምክንያት ሙያችንን ማሳደግ አልቻልንም ሲሉም ባለሙያዎች ተደምጠዋል፡፡

የሆስፒታሉ ዋና ስራ አስኪያጅ ዶ/ር ጂብሪል አባስ እንደገለጹት በተቋሙ መሰጠት ካለበት 6 የራዲዮሎጂ አገልግሎቶች በአሁኑ ስአት እየተሰጠ ያለው የ2ቱ ብቻ በመሆኑ ተገልጋዮች የሌሎቹን አገልግሎት ለማግኘት ወደ ሌላ አከባቢ በሚሄዱበት ጊዜ በአከባቢው በሚታየው የመሰረተ ልማት አለመሟላት ምክንያት  ለበለጠ እንግልት እየተዳረጉ እንደሆነ ጠቅሰው በሆስፒታሉ ያለው የታካሚዎች እና የአልጋ ቁጥር አለመመጣጠን ለአገልግሎት አሰጣጣችን እንቅፋት ሆኖብናል ብለዋል፡፡

ማህበረሰቡ በቂ የፋርማሲ አገልግሎት እንዲያገኝ በአከባቢው የከነማ ፋርማሲ ሊከፈት እንደሚገባ ያመላከቱት የሆስፒታሉ ዋና ስራ-አስኪያጅ  ከመድሃኒት፣ ከህክምና መሳሪያዎች እንዲሁም ከቦታ ማስፋፋት ጋር ተያይዞ ያጋጠሙንን ችግሮች ለመቅረፍ የከተማ መስተዳድሩ፣ የጤና ጽ/ቤቱ እና የቋሚ ኮሚቴው ድጋፍ ያስፈልገናል ብለዋል፡፡

ቋሚ ኮሚቴው በበኩሉ ሆስፒታሉ ባለው ክፍል ልክ ለሕብረተሰቡ አገልግሎቱን መስጠት መቻሉን በጥንካሬ አንስቶ ያጋጠመውን የህክምና መሳሪያዎች እጥረት ሊፈታና በቦታ ጥበት ምክንያት አገልግሎት ሳይሰጡ የተቀመጡ መሳሪያዎችን አገልግሎት እንዲሰጡ በማድረግ በተገልጋዩ ህብረተሰብ ላይ እየደረሰ ያለውን ለእንግልት ለማስቀረት በትኩረት ሊሰራ ይገባል ሲል አስገንዝቧል፡፡