null 60th Extraordinary Session of the IGAD Council Addressed

የሶስቱን አዋጆች መጽደቅ አስፈላጊነት በተመለከተ የውሳኔ ሃሳብና ሪፖርት ያቀረቡት  የህግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ጴጥሮስ ወልደ ሰንበት በአዋጆቹ ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር ሰፊ ውይይት እንደተደረገባቸው ለምክር ቤቱ አብራርተዋል፡፡

 

የኢፌዴሪ ባህልና ቱሪዝም ሚንስቴር ሚኒስትር ወ/ሮ ሂሩት ወልደማሪያም እንደገለጹት ቅርሶች በተፈጥሮ፣ በእድሜ ብዛት እና በሰው ሰራሽ አደጋዎች ጉዳት እንዳይደርስባቸው በግማሽ ዓመቱ ለ10 ቅርሶች የጥበቃና እንክብካቤ ስራዎች ለማከናወን በታቀደው መሰረት ለ10ም ቅርሶች ጥበቃና እንክብካቤ ማድረግ ተችሏል ብለዋል፡፡

የውስጥና የውጭ አገር ቱሪስቶች ስለ አገሪቱ ታሪክና ባህል ግንዛቤ እንዲኖራቸው ቅርሶችን በቋሚና ጊዜያዊ ኤግዚቢሽን አደራጅቶ ለእይታ እንዲውሉ በታቀደው መሰረት ከአውሮፓ ህብረት የባህል ለልማት ፕሮጀክት ጋር በመተባበር የሰው ዘር ምንጭ ሙዝየም የህንፃ ዲዛይን ስራው ሰፊ ውይይት ተደርጎበት ርክክብ እንደተፈጸም ሚኒስትሯ ተናግረዋል፡፡

የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ወ/ሮ ሂሩት ወልደ ማሪያም ምላሽ በሰጡበት ወቅት የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያንን ጨምሮ አደጋ ላይ ላሉት የሀገሪቱ ቅርሶች እንደ ጉዳታቸው ሁኔታ በባለሙያ እየታየ ጥገና እየተደረግላቸው መሆኑን ያስረዱ ሲሆን፤ የውስጥና የውጭ መልካም አስተዳደር ችግሮችን ለይቶ ከመፍታት አንጻር ርብርብ ቢደረግም አሁንም ውስንነት መኖሩን ሚኒስትሯ ተናግረዋል፡፡