null The Austrian Delegates said, Women’s participation in executive bodies has a significant role to ensure the reform.

በአስፈጻሚ አካሉ ውስጥ የሴቶች ተሳትፎ  ከፍተኛ መሆኑ ሃገሪቱ የጀመረችውን ለውጥ ለማስቀጠል ሚናው የጎላ እንደሆነ የኦስትሪያ የልዑካን ቡድን ገለጸ፡፡

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ- ጉባኤ ወ/ሮ ሽታዬ ምናለ የልዑካን ቡድኑን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡

የውይይቱ ዋና አላማ በሁለቱ ሃገራት መካከል ያለውን ሁለንተናዊ የሆነ የሁለትዮሽ ግንኙነቱን አጠናክሮ ለማስቀጠል ያለመ መሆኑን ምክትል አፈ- ጉባኤ ወ/ሮ ሽታዬ አብራርተዋል፡፡

በውይይታቸው ወቅት በሃገሪቱ እየተካሄዱ ስለሚገኙ ስነ-ምጣኔ ሃብታዊ ፣ ማህበራዊ ፣ ፖለቲካዊ እና በስደተኞች ዙሪያ   ትኩረት አድረገው ተወያይተዋል፡፡

መንግስት   የስነ-ምጣኔ ሃብት ዘርፍን  ለማሳደግ ስትራቴጂ ነድፎ እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ የጠቀሱት ወ/ሮ ሽታዬ፤ የኢንዱስትሪያል ፓረኮች፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድና ኢትዮ ቴሌኮም እንዲሁም የስራ እድል ፈጠራ ትኩረት  ከተደረገባቸው ዘርፎች  መካከል ተጠቃሾ  እንደሆኑ አብራርተዋል፡፡

ሃገሪቱ ከተለያዩ ሃገራት የሚመጡ ስደተኞችን ተቀብላ እያስተናገደች እንደመትገኝ የገለጹት ምክትል አፈ-ጉባኤዋ፤ ለዚህ ማሳያም ምክር ቤቱ ስደተኞችን የሚመለከት አዋጅ እንዳጸደቀ ለልዑካን ቡድኑ ጠቅሰዉላቸዋል፡፡

የኦስትሪያንና የኢትዮጵያን የሁለትዮሽ ግንኙነት ከመቸውም ጊዜ በበለጠ ሁኔታ ለማሳደግ ኢትዮጵያ  በቬና ኢምባሲዋን ለመክፈት በዝግጅት ላይ እንደምትገኝ የውጭ ግንኙነትና ሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ  አቶ ተስፋዬ ዳባ ገልጸው፤ የሁለቱን ሃገራት ስነ-ምጣኔ ለማሳደግ የአየር ትራንስፖርት  ድርሻው ከፍተኛ ስለሆነ  በዘርፉ ላይ በትኩረት መስራት እንደሚገባም ለልዑካን ቡድኑ  አክለው ተናግረዋል፡፡

የኦስትሪያ የልዑካን ቡድን በትምህርት፣ በግብርና ፣ በስነ-ምጣኔና  የፓርላሜንታዊ ግንኙነቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጾ፤ ለኤምባሲው መከፈትም የኦስትሪያ መንግስት ድጋፍ  እንደሚያደርግ  ገልጸዋል፡፡

መንግስት በአስፈጻሚ አካሉ ውስጥ የሴቶች ተሳትፎ 50 በመቶ እንዲሆን መወሰኑ የልዑካን ቡድኑ  አድንቆ፤ ሃገሪቱ በትክክለኛ የዴሞክራሲ ጎዳና ላይ እንደምትገኝ አንዱ ማሳያ መሆኑና ይህም ሃገሪቱ ለጀመረችው የለውጥ እንቅስቃሴ ሚናው ከፍተኛ እንደሆነ አስተያየታቸውን ገልጸዋል፡፡

ሃገራችን ያለችበት የሰላም ሁኔታ ለኢንቨስትመንት ምቹ ስለሆነ የኦስትሪያ ባለ ሃብቶች ወደ ሃገራችን መጥተው በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ተሰማርተው ኢንቨስት እንዲያደረጉ ግፊት ማድረግ እንዳለባቸው ወ/ሮ ሽታዬ የልዑካን ቡድኑን

 አሳስበዋል፡፡