null The House approved the establishment of national elctorial board and varius bills.

ምክር ቤቱ የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ማቋቋሚያ አዋጅን ጨምሮ የተለያዩ አዋጆችን አጸደቀ፡፡

መጋቢት 27 /2011 ዓ.ም፤ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው 4ኛ ልዩ ስብሰባው ለረቂቅ አዋጁ የተዘጋጀውን ሪፖረትና የውሳኔ ሃሳብ አድምጦ ስድስት የተለያዩ አዋጆችን መርምሮ አጽድቋል፡፡

ምክር ቤቱ የኢፌዴሪ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅን በተመለከተ  በህግ፣ ፍትህና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የቀረበለትን ሪፖርትና የውሳኔ ሃሳብ መርምሮ አዋጁን  አጽድቋል፡፡

አባላቱ  በረቂቅ አዋጁ ውስጥ በተካተቱ ሃረጎች ዙሪያ በዝርዝር ከተወያየና በተናጠል ድምጽ ከሰጠ በኋላ አዋጁን  በአብላጫ ድምጽና በአራት ድምጸ-ተዓቅቦ አጽድቆታል፡፡

አዋጁ ጠንካራ፣ ገለልተኛና ተዓማኒ የሆነ የምርጫ አስፈጻሚ ተቋም ለማደራጀት ምቹ የሆነ የህግ ማዕቀፍ እንዲኖር የሚያስችል መሆኑና የቦርድ አባላት የሚመለመሉበትና ለሹመት የሚበቁበት አሰራር ግልጽና የባለድርሻ አካላትን ተሳትፎ ያረጋገጠ አዋጅ መሆኑን የህግ፣ ፍትህና ዴሞኪራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚ ስብሳቢ ወ/ሮ ፎዚያ አሚን አብራርተዋል፡፡

 በተመሳሳይ ምክር ቤቱ በኢፌዴሪ መንግስትና በጣሊያን ሪፐብሊክ መንግስት መካከል ለአነስተኛና መካከለኛ ከተሞች ሳኒቴሽን መስረተ ልማት ማስፋፊያና ማሻሻያ ፕሮግራም ከፊል ማስፈጸሚያ በተመለከተ  በገቢዎች፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የቀረበለትን ሪፖርትና የውሰኔ ሃሳብ መርምሮ የብድር ስምምነት አዋጁን በሙሉ ድምጽ አጽድቋል፡፡

ብድሩ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ነዋሪዎች በሚገኙባቸው በስድስት አነስተኛና መካከለኛ ከተሞች  አካባቢዎች ያለውን ሳኒቴሽን አገልግሎት በማሻሻል በእነዚህ አካባቢዎች የሚገኙ የህበረተሰብ ክፍሎች ጥራት ያለው የሳኒቴሽን አገልግሎት ተጠቃሚ የሚያደርግ አዋጅ መሆኑን  የገቢዎች፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ  ሰብሳቢ ወ/ሮ ለምለም ሃድጎ ገልጸዋል፡፡

የተገኘው ብድር ከወለድ ነጻ፣ የ20 ዓመታት የችሮታ ጊዜን ጨምሮ በ30 አመታት ውስጥ ተከፍሎ ሚያቅልና ከሃገራችን የብድር ስትራቴጂ ጋር  የተጣጣመ መሆኑን ወ/ሮ ለምለም አክለዋል፡፡

ምክር ቤቱ አክሎም በኢፌዲሪ መንግስት እና በጣሊያን ሪፐብሊክ  መካከል የተደረገውን ለዘላቂና አካታች የግብርና ምርት እሴት ሰንሰለት እድገት ፕሮግራም  ማስፈጸሚያ በተመለከተ  በገቢዎች፣ በጀትና ፋይናንስ  ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ  የቀረበለትን ሪፖርትና የውሳኔ ሃሳብ መርምሮ  የብድር ስምምነት  አዋጁን  በሙሉ ድምጽ አጽድቋል፡፡

ፕሮጀክቱ የግብርና ምርቶችን ምርትና ምርታማነትን ለማሻሻል የሃገር ውስጥ የምግብ ፍጆታን የሚያሟላና የአግሮ-ኢንደስትሪ የምርት ቅብብሎሽን በማሳደግ የውጭ ገበያ አቅርቦትን ከፍ በማድረግ ረገድ አስተዋጾው ከፍተኛ መሆኑን ሰብሳቢዋ ወ/ሮ ለምለም ገልጸዋል፡፡

ብድሩ ከወለድ ነጻ ሆኖ የ6አመታት የችሮታ ጊዜን ጨምሮ በ30 አመታት ውስጥ ተከፍሎ የሚያልቅ እንደሆነ ተብራርቷል፡፡

እንዲሁም ምክር ቤቱ በኢፌዲሪ መንግስትና በአለም አቀፉ የልማት ማህበር መካከል ለዘላቂ መሬት አያያዝ  ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ በተመለከተ በገቢዎች፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ   የቀረበለትን የውሳኔ ሃሳብ መርምሮ አዋጁን   በሙሉ ድምጽ አጽድቋል፡፡

ፕሮጀክቱ በስድስት ክልሎች ማለትም በኦሮሚያ፣ አማራ፣ ትግራይ፣ ቤንሻንጉል ጉሙዝ ፣ ጋምቤላና ደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልሎች ውስት ባሉ 157 ወረዳዎች ውስጥ ከዚህ በፊት የተከናዎኑ እንቅስቃሴዎችን ለማስቀጠልና ለ645 ሽህ እማ/አባዎራዎች ቀጥተኛ ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ወ/ሮ ለምለም  ከጠቀሷቸው መካከል አንዱ  ነው ፡፡

 በመቀጠልም ምክር ቤቱ በኢፌዲሪ መንግስትና በቻይና እክስፖርት-ኢምፖርት ባንክ መካከል ለመቀሌ ውሃ  አገልግሎት አቅርቦት ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ በተመለከተ  በገቢዎች፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የቀረበለትን ሪፖርትና የውሳኔ ሃሳብ መርምሮ  የብድር ስምምነት ለማጽደቅ የቀረበለትን  አዋጅ በሙሉ ድምጽ አጽድቆታል፡፡

ፕሮግራሙ የመቀሌ ከተማ የውሃ አገልግሎት እያደገ የመጣውን የነዋሪውን ህዝብ የውሃ ፍላጎት ሊያረካ ያልቻለ በመሆኑ የከተመዋ ሰፊ ንጹህ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ችግር ለማቃላል የሚያስችል ስምምነት መሆኑን ወ/ሮ ለምለም ጠቅሰዋል፡፡

ከቻይና ኤክስፖርት -ኢምፖርት ባንክ የተገኘዉ የብድር ገንዘብ  229,784,582.04 የአሜሪካን ዶላር ነዉ ።

በመጨረሻም ምክር ቤቱ የ2011 በጀት አመት ተጨማሪ በጀት ረቂቅ አዋጅን በተመለከተ  በገቢዎች፣ በጀትና ፋይናነንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የቀረበለትን ሪፖርትና ውሳኔ ሃሳብ መርምሮ 33,986,693,730/ ሰላሳ ሶስት ቢሊዮን ዘጠኝ መቶ ሰማንያ ስድስት ሚሊዮን ስድስት መቶ ዘጠና ሶስት ሽህ ሰባት መቶ ሰላሳ ብር / ተጨማሪ ወጪ መጠባበቂያ በጀት በጀት ሆኖ በአብላጫ ድምጽና በአንድ ድምጸ ተአቅቦ ጸድቋል፡፡ 

የበጀት ምንጩ ከሃገር ውጭ ከአለም አቀፍ የልማት ማህበር በቀጥታ ድጋፍ ፣ በእርዳታና በበድር የተገኘ ገቢ ሲሆን በሃገራችን በተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋ የሚከሰተውን ጉዳት ለመከላከልና ለመቋቋም እንዲሁም በ2011 በጀት አመት የተቀመጡ የፕሮግራም በጀት ግቦችን ለማሳካት እንደሆነ ወ/ሮ ለምለም  ከጠቀሷቸው መካከል ተጠቃሹ ነው፡፡