null The House of People's Representatives has reviewed and approved the draft state of emergency issued by the Council of Ministers.

ም/ቤቱ 5ኛ ዙር 5ኛ አመት 2ኛ ልዩ ስብሰባውን ዛሬ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት አዳራሽ አካሄዷል፡፡

ሚያያ 02/2012 ዓ/ም ዜና ፓርላማ፡- ምክር ቤቱ ዛሬ ባካሄደው ልዩ ስብሰባ የሚኒስትሮች ምክር ቤት መጋቢት 3ዐ ቀን 2012 ዓ/ም ባካሄደው ስብሰባ የኮረና ቫይረስ ወረርሽኝ ሥርጭትን ለመከላከል፣ ለመቆጣጠርና የሚያስከትለውን ጉዳት ለመቀነስ ያወጣውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለማጽደቅ  የቀረበውን ረቂቅ  አዋጅ መርምሮ አጽድቋል፡፡

በቀረበው ረቂቅ አዋጅ  የምክር ቤት አባላት ሰፊ ውይይት ካደረጉ በኃላ በተደረሰው ስምምነት መሠረት  የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቁጥር 1189/2012  በመሆን በአንድ ድምፅ ታአቅቦ በአብላጫ ድምፅ ፀድቋል፡፡

በተጨማሪም ሰባት አባላትን ያካተተ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈፃፀም መርማሪ ቦርድ ም/ቤቱ ሰይሟል፡፡

የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ ተገሠ ጫፎ  እጩ የቦርድ አባላትን ለምክር ቤቱ ያቀረቡ ሲሆን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈፃፀም መርማሪ ቦርድ አባል በ12 ተቃውሞ በ5 ድምፅ ተአቅቦ በአብላጫ ድምፅ በውሳኔ ቁጥር 6/2012 ፀድቋል፡፡  ተሻóሚዎች ቃለ-መሃላ ፈጽመዋል፡፡

ም/ቤቱ በኢትዮጵያና በአለም አቀፍ የልማት ማህበር መካከል ለኮረና ቫይረስ አስቸኳይ ጊዜ ምላሽ ኘሮጀክት ማስፈፀሚያ የ82 ሚሊዮን 6 መቶ ሺ የአሜሪካ ዶላር የተፈረመ የብድር ስምምነትን አጽድቋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ለፌደራል መንግስት የ2ዐ12 በጀት አመት የ|ሚውል አንድ ነጥብ ሁለት ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር የቀረበውን ተጨማሪ በጀት ረቂቅ አዋጅ ቁጥር 1188/2012 በመሆን ፀድቋል፡፡

በተመሣሣይ ምክር ቤቱ ዛሬ ባካሄደው ልዩ ስብሰባው በኢትዮጵያና በአለም አቀፍ የልማት ማህበር መካከል ለሁለተኛው የኢትዮጵያ የእድገትና ተወዳዳሪነት የልማት ማስፈፀሚያ የቀረበውን የብድር ስምምነት ረቂቅ አዋጅ በአዋጅ ቁጥር 1191/2012 ያፀደቀ ሲሆን  ለአፍሪካ የበሽታ መቆጣጠርና መከላከያ ማዕከል ክፍለ አህጉራዊ ኢንቨስትመንት ኘሮጀክት ማስፈፀሚያ የተደረገ የብድር ስምምነት የቀረበ ረቂቅ አዋጅን በአዋጅ ቁጥር 1192/2012 መርምሮም አጽድቋል፡፡