null The Kalliti –Tullu Dimttu road construction is delayed.

ከቃሊጢ ቱሉ ዲምቱ የሚገነባው የመንገድ ፕሮጀክት ግንባታ ግንባታው እየተጓተተ ነው ተባለ፡፡

በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የገቢ፣የበጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የፕሮጀክቱን ግንባታ የመስክ ምልከታ አካሂዷል፡፡

ቀን መጋቢት 24| 2011 ዓ.ም ቋሚ ኮሚቴው አጠቃላይ ግንባታው በምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝና የግንባታው ገጽታ ምን እንደሚመስል  ከፕሮጀክቱ ሰራተኞች ጋር በመሆን የተሰሩትንና እየተሰሩ የሚገኙትን  ስራዎች  እየተዟዟረ ከጎበኘ በኋላ በተያዘለት ጊዜ መጠናቀቁንና አለመጠናቀቁንም  አካላዊ ግምገማ በማድረግ ውይይት አካሂዷል፡፡

የመንገዱ ፕሮጀክቱ ግንባታ የተጀመረው ሚያዚያ 2009 ዓ.ም ሲሆን መጠናቀቅ ያለበት ደግሞ ሚያዚያ 2012 ዓ.ም  እንደሆነ ቋሚ ኮሚቴው ከሰራተኞች ጋር ባካሄደው ውይይት መረጃ ቢያገኝም እስከ ሁለት ዓመት 70% ለማድረስ ቢታቀድም  32% ብቻ እንደደረሰ ቋሚ ኮሚቴው አረጋግጧል፡፡

ቋሚ  ኮሚቴው  የፕሮጀክቱን  ግንባታ አምና ካደረግው የመስክ ምልከታ ዘንድሮ የተሻለ እንቅስቃሴ ቢኖረውም  የተፈለገውን ያህል እየሄደ እንዳልሆና በዚህ የሚቀጥል ከሆነ ግን በተያዘለት ጊዜ ይጠናቀቃል ለማለት ያሰጋል ብሏል፡፡

የካሳ ክፍያ በተለይ የመኖሪያ ቤቶችንና የንግድ ቤቶችን ከክፍለ ከተማ ና ከከተማ አስተዳደ ጋር በጋራ በመሆን  ችግሩ ስለተፈታ  እጅግ በጣም ትልቅ ስኬት ፣  500 የሚሆኑ ወጣቶች በፕሮጀክቱ ውስጥ ገብተው የስራ እድል ተፈጥሮላቸው  ስራ መስራታቸው የሚሉትና ከከተማ አስተዳደሩ ለፕሮጀክቱ ግንባታ የሚውል የበጀት እጥረት እንዳይኖር ቅድመ ዝግጅት ማድረጉ የተሻሉ ስራዎች እንደሆኑ ቋሚ ኮሚቴው  በጥሩ ጎኑ አንስቷል፡፡

የክፍያ መዘግየት፣የውሃና ፍሳሽ ቱቦዎችን ማንሳት ትልቅ ተግዳድሮት መሆን፣በፕሮጀክቱ አካባቢ ያሉ የመብራት ፖሎች አለመነሳታቸውና ከሚመለከተው አካል ጋር በቅንጅት ከመስራት አኳያ  ውስንነት  መኖሩ በእጥረት ቋሚ ኮሚቴው አንስቶ ቀጣይ ሊስተካሉ እንደሚገባ  በአጽንኦት አሳስቧል፡፡

የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣና ዋና ዳይሬክተር ኢንጅር ሞገስ ጥበቡ ለፕሮጀክቱ ይበልጥ አንገብጋቢ ነው በማለት በቻይና ኤግዚን ባንክ በዚህ ዓመት መከፈል የነበረበት 650 ሚሊዮን ብር ከተማ አስተዳደሩ በትብርና በተለየ ሁኔታ በካቢኒ ደረጃ በመወሰኑ ትልቅ አበረታች  እንደሆነ አስገንዝበዋል፡፡

በመጀመሪያው ወቅት አካባቢ ብዙ ጊዜ  የሚፈጅብን ግን የገንዘብ መጠናቸው ትንንሽ  የሆኑ ስራዎች  ይሰሩ እንደነበረና አሁን የአስፋልትና ተያያዥ የሆኑ ስራዎች በአጭር ጊዜ ብዙ መስራት የሚቻል ግን የገንዘብ መጠናቸው ብዙ ስለሆነ ስራዎች በተፈለገው ልክ እንዳንሄዱ ትልቅ ማነቆ ሁኖ ሲያጋጥማቸው እንደነበር  ኢንጅነሩ ለቋሚ ኮሚቴው አስረድተዋል፡፡

በገንዘብ ሚኒስቴር በኩል የተለየ ድጋፍና ክትል እየተደደረገላቸው እንደሆነና ባንኩም በተለየ ሁኔታ ትኩረት ሰጥቶ መፍትሄ እንዲሰጥ በተዳጋጋሚ ብናናግረውም በአገር አቀፍ ደረጃ የሚፈታ ጉዳይ ስለነበር በአጭር ጊዜ እንደሚፈታ ተስፋ ሰጭ ምልክቶች እንዳሉ አውቀናል ብለዋል ዋና ዳይሬክተሩ፡፡

በፕሮጀክቱ ውስጥ ከ387 በላይ  ቤቶች፣አጥሮችና ተያያዥ ጉዳይ እንደነበሩና 265 ጉዳዮች በክፍለ ከተማው አስተዳደር ርብርብ ተደርጎ ችግሩ መፈታን ዋና ዳይሬክተሩ ኢንጅነር ሞገስ  ጠቅሰው በውሃ ና ፍሳሽ በኩል ትልቅ ፈተና ሲያጋጥማቸው እንደነበርና 800 ሚሊ ሊትር ዲያሜትር ያለው ከአቃቂ ጀምሮ ወደ መሃል ከተማ ይሄድ የነበረው ዋና መስመር ለማንሳት በጫራታ ሂደት ላይ እንደነበርና በታሰበው መንገድ የመንገዱን የግራ ክፈል ለመስራት ትልቅ ፈተና ሁኖ እንደቆየና አሁን ባለው ሁኔታ ይህንን የሚያነሳ የስራ ተቋራጭ ውለታ ተፈራርመናል ብለዋል፡፡

 

 የአዲስ አበባ የውሃ ና ፍሳሽ ባለስልጣን  መስሪያ ቤት  ፕሮጀክቱ በሚሰራበት አካባቢ ከ131 በላይ የውሃ ፍሻ ቶቦች ስላሉ  ችግሩን በመገንዘብ  ቱቦዎችን በማንሳት ሊተባበራቸው እንደሚገባና ቋሚ ኮሚቴው የበኩሉን ድርሻ ሊወጣ ይገገባል ብለዋል ዋና ዳይሬክተሩ፡፡