null The over all performance of Ethiopian National Acredation secretariat is insufficient.

የኢትዮጵያ ብሔራዊ አክሬዲቴሽን ጽህፈት ቤት አጠቃላይ አፈጻጸሙ ዝቅተኛ መሆኑ ተገለጸ፡፡

ሚያዚያ 14 ቀን 2011 ዓ.ም የኢፌደሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ንግድና ኢንዱስትሪ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የኢትዮጵያ ብሔራዊ አክሬዲቴሽን ጽህፈት ቤት የ9 ወር የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ተወያይቷል፡፡

 በውይይቱ የጽህፈት ቤቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ አርአያ ፍሰሃ ለሕክምና ላቦራቶሪ አክሬዲቴሽን በአለም አቀፍ ስታንዳርድ  መሰረት አክርዴትድ ማድረግ /እዉቅና ለመስጠት  28 ታቅዶ 12 መደረጉን፣ በተመሣሣይም በፍተሻና በካሊብሬሽን ላቦራቶሪ አክርዴትድ ማድረግ  / ለ7 እዉቅና መስጠት  ታቅዶ 4 መከናወኑን ገልጸዋል፡፡

በሰርተፊኬሽን የአክርዲቴሽን አገልግሎት  የ2   አመልካቾችን  ሰነድ  መሟላቱን  የገመገሙ መሆኑን፣ በኢንስፔክሽን  የአክርዲቴሽን  አገልግሎት መስጠት በአለም አቀፍ ስታንዳር መሰረት የአክሬዲት ማድረግ 6 ታቅዶ 5 መደረጉን አብራርተዋል፡፡ በአዲሱ ISO/IEC 17011፡ 2017 መስፈርት  መሰረት ሁሉም ሰነዶች መከለሳቸውንና በህብረተሰቡ ዘንድ የአክርዲቴሽን ግንዛቤ ለማሳደግ የተለያዩ ስልጠናዎች መሰጠታቸውን ዋና ዳይሬክተሩ አብራርተዋል፡፡

አክሬዲትድ የሆኑ የካሌብሬሽን ወሰኖች ዉስንነነት እና የተቆጣጣሪ ባለስልጣናት የተስማሚነት ምዘና አካላት ወደ አክረዲቴሽን እንዲመጡ የሚያደርጉት ጥረት ዉስንነትና አክሬዴት የሆኑና ያልሆኑትን አለመለየት ካጋጠሙ ችግሮች ዋናዎቹ መሆናቸውን አንስተዋል፡፡ ተቆጣጣሪ አካላትም ዕውቅና ያገኙትን በመለየት የማበረታታትና ቅድሚያ ገበያ የሚያገኙበትን ሁኔታ ማመቻቸት ቢችሉ  የተሻለ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

ቋሚ ኮሚቴው የተሰጡ የተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎች፣በህክምና ላብራቶሪ ፍተሻ ላይ ሰነድን ተቀብሎ መመርመሩ፣በአዲሱ መስፈርት መሰረት ሰነዶችን መከለሱን እንዲሁም ዕውቅና መስጠትና ኢንስፔክሽን በሚመለከት የተሰሩ ስራዎች በጥሩ ጎን አንስቷል፡፡

 በሌላ በኩል አብዛኞቹ ተግባራት ከሂደት ያለፉ አለመሆናቸው በእጥረት ተመልክቶ ከባለድርሻ አካላት ጋር በሆን ተቋማት ዕውቅና እንዲያገኙ ለማድረግ ግፊት ማድረግና ድጋሚ ፍተሻ  በማድረግ ጊዜ ያለፈባቸው ዕውቅናዎችን መፈተሽና የዜጎችን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ እንደሚያስፈልግም ቋሚ ኮሚቴው ገልጿል፡፡በሁሉም ዘርፍ የተሠሩ ሥራዎች  አፈጻጸማቸው ዝቅተኛ  በመሆኑ ትኩረት ተሰጥቶ ሊሰራ እንደሚገባ ቋሚ ኮሚቴው አሳስቧል፡፡