null The Standing Committee discussed with political parties and other stakeholders on the deraft proclamation to establish the national elctorial board.

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የህግ ፍትህ እና ዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በፌደራል ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ ዙሪያ ከፖለቲካ ፓርቲዎች እና ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አደረገ፡፡

የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ህገ-መንግስታዊ ተልእኮውን ለመወጣት እንዲችል ያሉበትን ውስንነቶች እና የመፍትሄ አቅጣጫዎች በመለየት ከባለ ድርሻ አካላት ጋር በተደረገው ውይይት የስራ አመራር ቦርድ አባላት ሙሉ ጊዜያቸውን በቦርዱ ስራ የሚያሳልፉ ተሿሚዎች መሆናቸውን እና የቦርዱ ሃላፊነት የሚጠይቀውን የአመራር ብዛት ከግምት በማስገባት የተሿሚዎች ቁጥር ከ9 ወደ 5 መቀነስ መቻሉ ተገልጿል፡፡

በኢትዮጵያ ዲሞክራሲን ለማጠናከር ምርጫ ቦርድን ከማናቸውም አካል ነጻ አድርጎ በማደራጀት ፍትሃዊ ተአማኒ እና ሰላማዊ ምርጫ ለማስፈጸም የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አባላት አመላመል እና አሿሿም እንዲሁም የስራ አመራር የቦርድ አባላት አሰያየም አሳታፊነት እና ግልጸኝነትን አስመልክቶ በውይይቱ የተገኙት የፖለቲካ ፓርቲዎች እና ባለ ድርሻ አካላት ሰፊ ውይይት አድርገዋል፡፡