ይሳተፉ

ለሕዝብ ጥቅም ሲባል የመሬት ይዞታ የሚለቀቅበትን፣ ካሣ የሚከፈልበት እና ተነሺዎች መልሰው የሚቋቋሙበትን ሁኔታ ለመወሰን

መግቢያ
መንግስት ለሕዝብ አገልግሎት ከሚያከናውናቸው የልማት ሥራዎች መሬትን ለመጠቀም፣ የአገሪቱ ከተሞች ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደጉና የነዋሪዎቹም ቁጥር እየጨመረ በመሄዱ በከተሞች ፕላን መሠረት ለመኖሪያ ቤት ግንባታ፣ ለመሠረተ ልማት፣ የኢንቨስትመንትና ሌሎች አገልግሎቶች የሚውል የከተማ መሬትን መልሶ ለማልማት፣ እንዲሁም በገጠር ለሚከናወኑ የልማት ሥራዎች መሬት አዘጋጅቶ ለማቅረብ፣ የመሬት ይዞታ እንዲለቁ ለተደረጉ ባለይዞታዎች ተገቢና ተመጣጣኝ ካሣና የተነሺ ድጋፍ ለመክፈል ግምት ውስጥ መግባት የሚገባቸውን መሠረታዊ መርሆዎችን ለይቶ ለመወሰን፣ ካሣውን የመተመን፣ የመክፈል እና ተነሺዎችን መልሶ የማቋቋም ሥልጣንና ኃላፊነት ያለባቸውን አካላት በግልጽ ለይቶ ለመወሰን በማስፈለጉ ምክንያት እነዚህን ተግባራት በተሳካ ሁኔታ ለመፈፀም እንዲቻል ለሕዝብ ጥቅም ሲባል የመሬት ይዞታ የሚለቀቅበትን፣ ካሣ የሚከፈልበት እና ተነሺዎች መልሰው የሚቋቋሙበትን ሁኔታ ለመወሰን አዋጅ ቁጥር 1161/2011 መውጣቱ ይታወሳል፡፡ ሆኖም ግን አዋጁ ለልማት ተነሺዎች ከሚከፈለው የካሳ ክፍያ ጋር በተያያዘ የመሰረተ ልማት ገንቢው ተቋም ካሳ እንዲፈፅም፣ የወሰን ማስከበር ሥራዎችን እንዲያከናውን እንዲሁም መሠረተ ልማቱንም እንዲገነባ ማድረጉ አላስፈላጊ ጫና እና የጊዜ ብክነት እየፈጠረ ይገኛል፡፡

ይምረጡ