ይሳተፉ

የነዳጅ ውጤቶችን የግብይት ስርዓት ለመደንገግ የቀረበ ረቂቅ አዋጅ

የነዳጅ ውጤቶች ካላቸዉ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ፋይዳ አንጻር ስትራቴጂክ ምርቶች በመሆናቸዉ አቅርቦታቸው፣ ክምችታቸው፣ ስርጭታቸው፣ ደህንነታቸው፣ ጥራታቸው እና ዋጋቸው ዓለም አቀፍ ደረጃዎችን በጠበቀ እና በሰውና በእንስሳት ጤና፣ በንብረትና በአካባቢ ላይ ጉዳት በማያደርስ ሁኔታ መከናወኑን ማረጋገጥ አስፈላጊ በመሆኑ፤
ከአስመጪው ጀምሮ እስከ መጨረሻው ተጠቃሚ ድረስ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደገፈ፣ ቀልጣፋ፣ ግልጽ፣ አስተማማኝ፣ ፍትሀዊ እና ተደራሽ የአቅርቦት፣ የስርጭት እና የችርቻሮ የአሰራር ሥርዓት በመዘርጋት በነዳጅ ውጤቶች የግብይት ሰንሰለት ውስጥ እየታዩ ያሉ ሕገ-ወጥ ተግዳሮቶችን ለመቆጣጠር የሚያስችል ምቹ ሁኔታ መፍጠር አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በዘርፉ የተሰማሩ የነዳጅ ተቋማትና ባለሙያዎች ዓለም አቀፍ ልምድ በሚጠይቀው መሠረት በሚፈለገው የብቃት ደረጃ ላይ የሚገኙ መሆናቸውን ማረጋገጥ ደህንነቱ የተጠበቀና ሕጋዊ የነዳጅ ውጤቶች የግብይት ሥርዓት ለማስፈን የላቀ ጠቀሜታ ያለው በመሆኑ፤
በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግስት አንቀጽ 55(1) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡

ይምረጡ