ይሳተፉ

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅ

የኢኮኖሚ ወንጀል በሀገሪቱ ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ በመሆኑ ይህንን ወንጀል መከላከል እና መቆጣጠር አስፈላጊ በመሆኑ እና ማንኛውም ሰው ከሕገ-ወጥ ድርጊት ማንኛውንም አይነት የኢኮኖሚ ጥቅም ማግኘት እንዳይችል የሚያደርግ ስርዓት በሕግ መዘርጋት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፥
በወንጀል የተገኘ ንብረትን ማጥናት፣ መለየት፣ ማገድ፣ መያዝ፣ መመርመር፣ መክሰስ፥ ንብረት ማስተዳዳር እና መውረስን የሚመለከቱ በተለያዩ ሕጎች ተበታትነው የሚገኙ ድንጋጌዎች በአንድ የሕግ ማዕቀፍ ውስጥ በማምጣት እና ለሁሉም የወንጀል አይነቶች እንዲያገለግሉ በማድረግ ለመሰረታዊ የሕግና የአፈጻጸም ጥያቄዎች ወጥነት ያለውና በቂ መልስ የሚሰጥ ሕግ ማውጣት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
ምንጩ ያልታወቀ ንብረት በሀገሪቱ የግብር ስርዓት፣ የውጭ ምንዛሬ፣ የገንዘብ ዝውውር ስርዓት እና የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ላይ ከፍተኛ አሉታዊ ተጽእኖ እያሳደረ በመሆኑእና ያለው የህግ ማዕቀፍ በመንግስት እና በህዝባዊ ድርጅት ሰራተኞች ላይ ብቻ የተወሰነ በመሆኑ ችግሩን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የሚያስችል የተሟላ የህግ ማዕቀፍ ማውጣት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ፤
ኢትዮጵያ በወንጀል የተገኘ ንብረት ማስመለስን በተመለከተ ያጸደቀቻቸውን ዓለም አቀፍ ስምምነቶች በተግባር ለማስፈጸም እና በወንጀል ድርጊት የሚገኝ ንብረትን ማስመለስ፤ መውረስና ማስተዳደርን በተመለከተ ዓለም አቀፍ መለኪያዎችን የሚያሟላ የሕግ ማዕቀፍ እንዲኖር ማድረግ በማስፈለጉ፤
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ህገ መንግስት አንቀፅ 55 (1) መሰረት የሚከተለው ታውጇል፡፡

ይምረጡ