ይሳተፉ

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት አዋጅ ቁጥር 354/95 ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ

​​​​​​​የኢምግሬሽን ህግ አገራት ሉአላዊ ስልጣንን ተግባራዊ ከሚያደርጉባቸው ህጎች አንዱ እና ዋነኛው ሲሆን አገራት የተቀናጀ የድንበር ቁጥጥር ስርዓት በመዘርጋት ከሀገር የሚወጡ እና ወደ ሀገር የሚገቡት የሰዎች ቁጥጥር በማድረግ ህጋዊ የሰዎችን እንቅስቃሴ እንዲኖር የሚያስችል ነው፡፡ ህጉ በዋነኛነት ለዜጎችና ለውጭ አገር ዜጎች የጉዞ ሰነድ፣ ህጋዊ የይለፍ ፈቃደ (ቪዛ)፣ ጊዜያዊና ቋሚ የመኖሪያ ፍቃድ ስለሚሰጥበት አግባብ፣ በህግ የተከለከሉ ሠዎች በህገ-ወጥ መንገድ ከሀገር እንዳይወጡና ወደ አገር እንዳይግቡ ቁጥጥር የሚደረግበትን አግባብ በመደንገግ ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን በመቆጣጠር የሀገርን ብሄራዊ ደህንነትና ሉአላዊነትን ማረጋገጥ ነው፡፡
ሀገራችንም የራስዋን የኢሚግሬሽን ህግ አውጥታ በኢ.ፊ.ዲ.ሪ ሕገ መንግስት ከተቀመጡት መሰረታዊ መብቶች አንዱ የሆነው የመዘዋወር ነፃነቶች ለማሰከበር የሚያስችል ለኢትዮጵያዊንና ለውጭ አገር ዜጎች ሕጋዊ የጉዞ ሰነድ የሚሰጥበትን ፣ የውጭ ሀገር ዜጎች ህጋዊ የይለፍ ፈቃደ (ቪዛ) መያዛችውን ስለሚረጋገጥበት ሁኔታ፣ ጊዜያዊና ቋሚ የመኖሪያ ፍቃድ የሚሰጥበትንና የሚታደስበትን፣ በህግ የተከለከሉ ሠዎች በህገ-ውጥ መንገድ ከሀገር እንዳይወጡና ወደ አገር እንዳይግቡ ቁጥጥር የሚደረግበትን አግባብ ተቀምጧል፡፡
በስራ ላይ ያለው የኢሚግሬሽን አዋጅ ቁጥር 354/1995 የወጣው በ1995 በመሆኑ አዋጁ እረጅም ጊዜ የሆነው ከመሆኑ አንጻር ከጊዜ ለውጥ ጋር የመጡ ለውጦችን ለማስተነገድ እንዲቻል በተለይም ICAO ያወጣው የተቀናጀ የድንበር ቁጥጥር አስተዳደር አገራት የመንገደኛ ቅድመ ጉዞ መረጃ እና ምዝገባ ስርዓት እንዲዘረጉ የሚያስገድድ ስለሆነ አገራችንም አንዱዋ ፈራሚ አገር እንደመሆና፤ከዚህ ጋር የሚጣጣም ስርዓት እንዲኖራት ለማድረግ እና አዋጁን በማስፈጸም በተግባር ያጋጠሙ ችግሮችን መፍታት የሚያስችል ማሻሻያ ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ ረቂቅ ማሻሻያ አዋጅ ተዘጋጅቷል፡፡

ይምረጡ