የባንክ ስራ ረቂቅ አዋጅ - ረቂቅ ሕጎች
ይሳተፉ
የባንክ ስራ ረቂቅ አዋጅ
Tigist T, modified 10 Months ago.
የባንክ ስራ ረቂቅ አዋጅ
Padawan Posts: 29 Join Date: 15/03/18 Recent Posts
ባንኮች ገንዘብ በማሰባሰብ እና ወደተለያዩ የኢኮኖሚ ዘርፎች በማሰራጨት ለኢኮኖሚ ልማት ወሳኝ ሚና የሚጫወቱ በመሆናቸው እና በሀገሪቱ ኢኮኖሚ የክፍያና የሂሳብ ማወራረድ ሥርዓት ውስጥ ቁልፍ ቦታ የሚይዙ በመሆኑ፤
ጥንቃቄ በተዘጋጀ የሕግ እና የቁጥጥር ማዕቀፍ መሰረት የባንክ ዘርፍን ለውጭ ኢንቨስትመንት ክፍት ማድረግ የዘርፉን ተወዳዳሪነትና ውጤታማነት በማሻሻል ለዘላቂ የኢኮኖሚ ዕድገት አስተዋጽኦ ያደርጋል ተብሎ የሚታመን በመሆኑ፤
አዋጭነቱ ያበቃ እና መልሶ አዋጭ የመሆን ተስፋ የሌለው ተደርጎ የሚቆጠር ማንኛውም ባንክ ከፍተኛ የሥርዓት መናጋትን እና ኪሳራን በማያስከትል መልኩ እልባት ለመስጠት አስፈላጊ የሆኑ በርካታ የተለያዩ ሥልጣኖችን እና አማራጮችን ለእልባት ሰጪ ባለሥልጣን አካሉ ማለትም ለብሔራዊ ባንክ የሚሰጥ ውጤታማ የእልባት ሥርዓት መኖር አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤