ይሳተፉ

የአጠቃላይ ትምህርት ረቂቅ አዋጅ

Portal Admin, modified 6 Months ago.

የአጠቃላይ ትምህርት ረቂቅ አዋጅ

Youngling Posts: 16 Join Date: 22/01/18 Recent Posts
ትምህርት ከሰው ልጅ መብቶች በዋናት የሚጠቀስ እንደመሆኑ መጠን ይህ መብት በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ ሕገ-መንግሥት ድንጋጌዎች ዕውቅናና ትኩረት የተሰጠው ቢሆንም የትምህርት ጥራትን እና ተደራሽነትን እንዲሁም ፍትሃዊነትን ለማረጋገጥ አስቻይ ሁኔታን የሚፈጥር ህግ ባለመኖሩ፤

በሕገ-መንግሥቱ፤ ሀገራችን በተቀበለቻቸው የተለያዩ ዓለም አቀፍ ስምምነቶችና በቀረጸችው ፖሊሲ አጠቃላይ ትምህርት ለሁሉም ዜጎች በፍትሐዊነት ተደራሽ መሆኑን የማረጋገጥ ኃላፊነት የመንግሥት በመሆኑ፣

የትምህርትን ጥራት፣ አግባብነትና ፍትሐዊነት በተለይም የትምህርት ደረጃን የማውጣት ሃላፊነት የፌዴራል መንግስቱ በመሆኑና ይህንም ለማስፈጸም ሕግ ማውጣት በማስፈለጉ፣

የትምህርት አስተዳደርን ባልተማከለ አሠራር በማዋቀር መንግሥት፣ ኅብረተሰቡና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት ለትምህርት ልማት ተገቢውን እገዛ ማድረግ እንዲችሉ የሚያበቃ የሕግ ማዕቀፍ በማስፈለጉ፣
አጠቃላይ ትምህርትን የሚመለከቱ የተበታተኑ ሕጎችና ደንቦች የነበሩ ቢሆንም መንግሥት በሚከተለው የትምህርት ልማት አቅጣጫ ተቃኝቶ የወጣ ሁለንተናዊ የአጠቃላይ ትምህርት ሕግ የሌለ በመሆኑ፣
​​​​​​​

ይምረጡ