ይሳተፉ

የከተማ መሬትን በሊዝ ስለመያዝ የወጣ አዋጅ

Portal Admin, modified 6 Months ago.

የከተማ መሬትን በሊዝ ስለመያዝ የወጣ አዋጅ

Youngling Posts: 16 Join Date: 22/01/18 Recent Posts
መሬት የመንግሥትና የሕዝብ ንብረት ሆኖ የመሬት አጠቃቀም በህግ እንደሚወሰን በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 40 ንዑስ አንቀፅ (3) የተደነገገ በመሆኑ፤
በሀገሪቱ እየተመዘገበ ያለው ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት የከተማ መሬት ፍላጎትን በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ እንዲመጣ በማድረጉ፣ ይህንን ፍላጎት በአግባቡ ለማስተናገድ የሚያስችል የመሬት ሀብት አቅርቦት እና አስተዳደር ሥርዓት መዘርጋት በማስፈለጉ፤
ለተሳለጠ፣ ለውጤታማ፣ ለፍትሐዊና ለጤናማ የመሬትና መሬት ነክ ንብረት ገበያ ልማት፤ ቀጣይነት ለተላበሰ የነፃ ገበያ ሥርዓት መስፋፋት፣ ግልጽና ተጠያቂነት ለሰፈነበት እንዲሁም የመሬት ተጠቃሚውን መብቶችና ግዴታዎችን ለማረጋገጥ የሚያስችል የመሬት አስተዳደር ሥርዓት በመገንባት መልካም አስተዳደርን ማረጋገጥ አስፈላጊ በመሆኑ፤
በነባሩ ሕግ ያጋጠሙ የሕግ ክፍተቶችን ለማስተካከልና ሌሎች የሊዝ ሥርዓቱን ይበልጥ ዉጤታማ የሚያደርጉ ድንጋጌዎችን ማካተት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
እንዲሁም ሀገሪቱ ከደረሰችበትና ልትደርስበት የምትፈልገዉን የዕድገት ደረጃ ባገናዘበ መልኩ የበለጠ ፈጣንና ቀጣይነት ያለዉ ልማትን ለማረጋገጥ፤ ለኪራይ ሰብሳቢነት የሚያጋልጡ ክፍተቶችን ለመዝጋትና ዜጎችን ፍትሐዊ የሀብት ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ነባሩን አዋጅ በአዲስ አዋጅ መተካት አስፈላጊ በመሆኑ፤
​​​​​​​

ይምረጡ