ይሳተፉ

የእንስሳት ጤና እና ደህንነት አዋጅ

Portal Admin, modified 5 Months ago.

የእንስሳት ጤና እና ደህንነት አዋጅ

Youngling Posts: 16 Join Date: 22/01/18 Recent Posts
በዓለም አቀፍ ደረጃ ተዓማኒነት ያለው የእንስሳት ጤና አገልግሎት በማስፈን ወጪ ገቢና ተሻጋጋሪ በሆኑ እንስሳት፣ የእንስሳት ውጤቶች፣ ተወፅዖዎችና ቁሶች ዝውውር ላይ ወደ ሀገር ውስጥ ሊገቡ ወይም ወደ ሌላ ሀገር ሊዛመቱ የሚችሉ በሽታዎችን መከላከልና መቆጣጠር በማስፈለጉ፤
 በሀገራችን የሚገኙ የእንስሳት በሽታዎችን መከላከል፣ መቆጣጠርና ደረጃ በደረጃ ጨርሶ በማጥፋት የሰዎችን ሕይወትና ጤንነት ከእንስሳትና ከእንስሳት ውጤቶችና ተዋፅኦዎች አማካኝነት ወደ ሰው እና ከሰው ወደ እንስሳት የሚተላለፉ በሽታዎችን ለመከላከል የሚያስችል ሥርዓት መዘርጋት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
 የእንስሳት፣ የእንስሳት ውጤቶችና ተዋጽኦዎች ጥራትና ደህንነት አስገዳጅ መስፈርት እየሆነ በመምጣቱ ሀገራችን ያላትን የገበያ ድርሻ ለማስጠበቅና አዳዲስ ገበያዎች ውስጥ ዘልቆ ለመግባት የእንስሳት ልየታ፣ ምዝገባና ክትትል ሥርዓት መዘርጋት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤ እንስሳት ለሰው ልጅ ከሚያበረክቱት አስተዋጽኦ በላይ እንደሰው ስሜት ያላቸውና መሰረታዊ ፍላጎት እንዲሟላላቸው የሚሹ ፍጡራን በመሆናቸው በተለያየ ጊዜና ሁኔታ የሚደርስባቸውን የደህንነት ችግር ማሻሻልና መቅረፍ በማስፈለጉ፤
​​​​​​​

ይምረጡ