የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መከላከያ ሠራዊት አዋጅን ለማሻሻል የወጣ ረቂቅ አዋጅ - ረቂቅ ሕጎች
ይሳተፉ
የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መከላከያ ሠራዊት አዋጅን ለማሻሻል የወጣ ረቂቅ አዋጅ
Tigist T, modified 2 Years ago.
የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መከላከያ ሠራዊት አዋጅን ለማሻሻል የወጣ ረቂቅ አዋጅ
Padawan Posts: 29 Join Date: 15/03/18 Recent Posts
የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የመከላከያ ሠራዊት የአገሪቱን ሉዓላዊነት የሚያስከብር፣ የብሔሮች፣ የብሔረሰቦችና የሕዝቦችን ሚዛናዊ ተዋፅዖ ያካተተና ከፖለቲካ ድርጅቶች ወገናዊነት ነፃ በመሆን ተግባሩን እንዲያከናውን የተደራጀ መሆኑ፤ የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የመከላከያ ሠራዊት የሚመራበትንና ከተሙ ወቅታዊ ግዳጅ ጋር የሚጣጣም እንዲሁም የወደፊቱን ግዳጅ ታሳቢ ያደረገ የህግ ማዕቀፍ የሚያስፈልገው በመሆኑ፤ በሥራ ላይ ያለውን የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የመከላከያ ሠራዊት የህግ ማዕቀፍ ማሻሻልና ማጠቃለል አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
አስተያየት
በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መከላከያ ሠራዊት አዋጅላይ ያለኝ አስተያየት፡
በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መከላከያ ሠራዊት አዋጅላይ ያለኝ አስተያየት፡
አንቀጽ 4 ንዑስ አንቀጽ 1 አደረጃጀት በኃይል ቢገለጽ የተሻለ ነው፡፡ የኢፌዲሪ መከላከያ ሠራዊት በምድር ኃይል ፣ በአየር ኃይል ፣ በባህር ኃይል ፣ በሳይበር ኃይል ና በጠፈር/ስፔስ ኃይል ይደራጃል ቢባል፣
አንቀጽ 13 ንዑስ አንቀጽ 1 እና 2 ለሠራዊት አባላት ስለሚደረግ ማበረታቻ ከሰላሳ ዓመትና ከዚያ በላይ ብቻ የታጠረ በመሆኑ ወደፊት ወደ መከላከያ የሚገቡትን ወጣቶች የሚያበረታታ አይመሰለኝም፤ በተጨማሪም ማበረታቻው የማዕረግ ልዩነቶችን ሳያሳይ በደፈናው የተቀመጠ ነው፡፡
አንቀጽ 72 ስለ ውትድርና አገልግሎት ሜዳይና ሪባን ሲገልጽ የአሥር ዓመት አገልግለት አልተጠቀሰም፡፡ በሌላ መልኩ በአንቀጽ 6 ንዑስ አንቀጽ 3 ላይ የእጩ መኮንንነት ምልመላ ከሠራዊት አባላትና በቀጥታ ከሲቪል ህብረተሰብ ይካሄዳል ይላል፡፡ በተጨማሪም በአንቀጽ 11 ንዑስ አንቀጽ 2 ማንኛውም የሠራዊት አባል መኮንን ከሆነ በኋላ ወይም የልዩ ሙያ ባለቤት ከሆነ ቢያንስ ለ10 ዓመታት የማገልገል ግዴታ አለበት ይላል፣ ስለዘህ ከሲቪል ህብረተሰብ የተመለመለ እጩ መኮንን የ10 ዓመት አግልግሎት ከጨረሰ በኋላ የውትድርና አገልግሎት ሪባን አያስፈልገውም ወይ?