ይሳተፉ

የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ረቂቅ አዋጅ

Tigist T, modified 3 Months ago.

የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ረቂቅ አዋጅ

Youngling Posts: 24 Join Date: 15/03/18 Recent Posts
የአንድን ህግ ጥራት ከሚወስኑት ነገሮች አንዱ በየጊዜው ያሉ ማሀበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና
ፖሊቲካዊ ለውጦችን በመፈተሽ ማሻሻያ ማድረግ ነው፡፡ የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም
አዋጅ ቁጥር 456/1997 ታውጆ ስራ ላይ ከዋለ ጀምሮ 18 ዓመታት አካባቢ ተቆጥረዋል፡፡ በዚህ
ጊዜ ውስጥም አገሪቱ እያስመዘገበች ካለው የኢኮኖሚ ዕድገት ጋር ተያይዞ በዚያው ልክ የአርሶ፣
አርብቶና ከፊል አርብቶ አደሮች ገቢም እያደገ ስለመጣ በመሬት ላይ ያላቸውን መብት ማሻሻያ
እንዲደረግ የሚያስገድዱ ሁኔታዎች ተከስተዋል፡፡ በተጨማሪም በነባሩ አዋጅ ውስጥ የምዝገባና
ቅየሳ ስራዎችን ሊገዙ የሚችሉ ድንጋጌዎች ባለመኖራቸው በአገራችን በስፋት እየተከናወነ ያለው
የገጠር መሬት ምዝገባና ቅየሳ ስራ አንድ ወጥ ሆኖ በክልሎች እንዲተገበር የሚያስችል የህግ
ማዕቀፍ አልነበረም፡፡ በመሆኑም ይህንን ታሳቢ በማድረግ አጠቃላይ የሆኑና ክልሎችን ሊመሩ
የሚችሉ፤ በአገር አቀፍ ደረጃ መሰረታዊና የቅየሳና ምዝገባ ስራዎች አንድ ወጥ ሊያደርጉ
የሚችሉ ሃሳቦች በህጉ ውስጥ እንዲካተቱ የተለያዩ ስራዎች ተሰርተዋል፡፡

ይምረጡ