ምክር ቤቱ በ2014 በጀት አመት ረቂቅ በጀት ላይ ዝርዝር ውይይት አካሄደ

(ዜና ፓርላማ) ሰኔ 24 ቀን 2013 .ም፣ አዲስ አበባ፤ የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች /ቤት ዛሬ ባካሄደው 17 መደበኛ ጉባኤው በ2014 በጀት ዓመት ረቂቅ በጀት ላይ ባደረገው ዝርዝር ውይይት ለገንዘብ ሚኒስቴር የሥራ ኃላፊዎች የተለያዩ ጥያቄዎችን አንስቶ ተወያይቷል፡፡

የምክር ቤቱ አባላት እንዳሉትም የፌዴራል ዋና ኦዲተር በተለያዩ መስሪያ ቤቶች የገንዘብ ጉድለት እንዳለ በፌዴራል ዋና ኦዲተር በየዓመቱ ሪፖርት ስለሚያቀርብና አንዳንድ መ/ቤቶች ኦዲት አንደረግም የማለት አዝማሚያ እያሳዩ በመሆናቸው የገንዘብ ሚኒስቴር ለምን እርምጃ አልወሰደም? የሚሉ ጥያቄዎችን አንተስተዋል፡፡

በአገር ውስጥና ከውጭ አገር በሚገቡ ዕቃዎች ኢኮኖሚያዊ ምክንያት ሳይኖር ነጋዴዎች ዋጋ እየጨመሩ በመሆኑ ሕብረተሰቡ እያማረረ በመሆኑ ችግሩን ለመፍታት ሚኒስቴር መ/ቤቱ ምን እየሰራ እንደሆነም ጠይቀዋል፡፡

አባላቱ አክለውም የግንባታ ፕሮጀክቶች በመጓተታቸው ምክንያት ተጨማሪ ገንዘብ ስለሚጠይቁ፣ ከውጭ አገር በሚገኘው ብድር የግንባታ ፕሮጀክቶችን ማጠናቀቅ ምን ያህል አስተማማኝ ነው? የገንዘብ ሚኒስቴር የብድር መመሪያ ባለማውጣቱ የብድር ሥርዓቱ ችግር እንደነበረበት፤ የፌዴራል ዋና ኦዲተር ለምክር ቤቱ ባቀረበው ሪፖርት እንዲገለፅላቸውም ነው ያቀረቡት፡፡

በተጨማሪም የህዝብ ጥግግት ባለበትም ሆነ በሌለበት ቦታ የሥራ አጥ ቁጥሩ ተመሳሳይ በመሆኑ ሥራ አጥነት ሰው ሰራሽ እንደሆነ የሚያመላክት ሁኔታ ስላለ ችግሩን ለመፍታት ሚኒስቴር መ/ቤቱ በጥኩረት መስራት እንዳለበትም አሳስበዋል፡፡

በመጨረሻም  አንዳንድ የፌዴራል መስሪያ ቤቶች ለቢሮ ኪራይ ብዙ ገንዘብ ስለሚያወጡ መስሪያ ቤቶቹ የራሳቸውን ቢሮ እንዲገነቡ ለምን በጀት አልተያዘላቸውም? ሲሉም ጠይቀዋል፡፡

የገንዘብ ሚንስትሩ ክቡር አቶ አሕመድ ሽዴ በበኩላቸው በተለያዩ መስሪያ ቤቶች የገንዘብ ጉድለት መኖሩን ጠቁመው ችግሩን ለመፍታት መስሪያ ቤታቸው ቁጥጥር በማድረግ  ጉድለት በሚያሳዩ የሥራ ኃላፊዎች ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ ተናግረዋል፡፡

ሚኒስትሩ አክለውም ለፕሮጀክቶች የሚገኘው አብዛኛው ብድር አስተማማኝ ስለሆነ እንደማያሰጋ ገልጸዋል፡፡

አያይዘውም መንግሥት ገንዘብ የሚበደረው ከብሔራዊ ባንክ ሳይሆን ከትሬዠሪ ቢል በመሆኑ የዋጋ ንረቱን እንደማያባብሰው ለምክር ቤቱ አስረድተዋል፡፡

በተመሳሳይም የብድር መመሪያ አለመኖርን አስመልክቶ ለተነሳላቸው ጥያቄ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የብድር መመሪያ እንዳለው ጠቁመው ተጨማሪ መመሪያ የሚያስፈልግ ከሆነም ማውጣት እንደሚቻል ነው የተናገሩት፡፡

በመጨረሻም የኢኮኖሚ ምክንያት ሳይኖራቸው ዋጋ የሚጨምሩ ነጋዴዎችን ለመቆጣጠር የገበያ ውድድሩን በማዘመንና ምርታማነትን በማሳደግ መቆጣጠር እንደሚቻል ሚንስትሩ አስገንዝበዋል፡፡

በጋሹ  ይግዛው