null A delegation led by the Honorable Tegas Chaffo participated in the joint session of the African Caribbean, Pacific and European Union Parliament.

በተከበሩ አቶ ታገሰ ጫፎ የሚመራ ልዕካን ቡድን የአፍሪካ  ካርቢያን፣ ፓስፊክ እና የአውሮፓ ህብርት ፓርላማ ጥምር ጉባኤ ላይ ተሳትፏል፤

የአፍሪካ  ካርቢያን፣ ፓስፊክ እና የአውሮፓ ህብርት ፓርላማ ጥምር ጉባኤ ( ACP-EU JOINT PARLIAMENTARY ASSEMBLY) ለጠ/ሚ/ር ዶ/ር ዐብይ አህመድ የ2019 የኖቤል ሰላም ሽልማት አሸናፊ  ሆነው በመመረጣቸው የተሰማውን ደስታና የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፏል፡፡

በኢፊዴሪ የህዝብ ተወካች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ  የተከበሩ አቶ ታገሰ ጫፎ የሚመራ የኢትዮጵያ ፓርላማ ልዕካን ቡድን በብራስልስ ቤልጄም እ.ኤ.አ  15-16 ኦክቶበር 2019 ከአውሮፓ ፓርላማ ውጭ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴዎች ጋር  የአፍሪካ  ካርቢያን፣ ፓስፊክ እና የአውሮፓ ህብርት ፓርላማ ጥምር ጉባኤ ( ACP-EU JOINT PARLIAMENTARY ASSEMBLY)  በተካሄደው ጉባኤ ላይ ተሳትፏል፡፡

የልኡካን ቡድኑ በጉባኤው ላይ በንቃት የተሳተፈ ሲሆን፤ የተከበሩ አፈ- ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን የፖለቲካና የኢኮኖሚ ሪፎርም ትክክለኛ ገፅታ ገልፀዋል፤

የኢትዮጵያ መንግስት በቀጠናው የልማት ትብብርንና ውህደትን ለማምጣት እያደረገውን ጥረትና በተለይም ለሱዳንና ደቡብ ሱዳን የሰላም ሂደት ስኬት ያበረከተው አስተዋፅኦ እጅግ ከፍተኛ መሆኑን ነው አፈ ጉባኤው አክለው የገለጹት፡፡

የታላቁ  የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ እየተካሄ እንደሚገኝ  አፈ- ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ በንግግራቸው አንስተዋል፤ የግድቡ የግንባታ አላማም የኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጨት መሆኑን ለጉባኤው አስገንዝበዋል፡፡ ኢትዮጵያ የምስራቅ አፍሪካ አገራትን  በመንገድ፣ በባቡርና  በኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦትና ተጠቃሚነት ለማስተሳሰር በሚደረገው ጥረት  ተግታ እየሰራች እንደምትገኝም ነው የተናገሩት፡፡

የአፍሪካ  ካርቢያን፣ ፓስፊክ እና የአውሮፓ ህብርት ፓርላማ ጥምር ጉባኤ ( ACP-EU JOINT PARLIAMENTARY ASSEMBLY)   ተባባሪ ፕሬዚዳንትና የአውሮፓ ፓርላማ አባላት እንዲሁም የአፍሪካ  ካርቢያን፣ ፓስፊክ ቡድን/ ACP Group/ አባላት የኢፌዲሪ ጠ/ሚ/ር  ክቡር ዶ/ር ዐብይ አህመድ የ2019 የኖቤል የሰላም ሽልማት አሸናፊ  ሆነው በመመረጣቸው የእንኳን ደሳለዎ መልእክት አስተላልፈውላቸዋል፡፡

በተጨማሪም ጉባኤው  በሰብሳቢዎቹ አማካኝነት ለኢትዮጵያ ህዝብና   ለጠ/ሚ/ር  ክቡር ዶ/ር ዐብይ አህመድ  የእንኳን ደስአላችሁ  መልዕክት የያዘ መግለጫ   አስተላልፏል፡፡   መግለጫው ብራስልስ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኢንባሲ በኩል ለኢትዮጵያ መንግስት እንደሚተላለፍ ታውቋል፡፡ በ 'JPA' እና  'ACP'  ድረ-ገፆች   እንደሚለቀቅም ተገልጿል፡፡