null A parliamentary delegation from France meets its Ethiopian counterpart.

የፈረንሳይ የፓርላማ ልዑክ ቡድን በጤናና በአቅም ግንባታ ዘርፍ ከኢትዮጵያ ፓርላማ ቡድን አባላት ጋር በጋራ እንደሚሰራ ተገለጸ፡፡    

የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የማህበራዊና የውጭ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴዎች የፈረንሳይ ፓርላማ ልኡካን ድንን ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡

የአገሪቱን የጤና ፖሊሲ ሁሉንም የጤና ፓኬጆችን ተደራሽ ለማድረግ የጤና ኤክስቴንሽኖችን በማስፋፋት፣ በሽታን የመከላከል አቅምን በማሳደግ፣ በህብረተሰቡ የሚከሰቱ ተዛማችና መሰል በሽታዎችን መግታትን ተቀዳሚ ተግባር አድጎ እየሰራ መሆኑን ቋሚ ኮሚቴዎቹ ከፈረንሳይ ለመጡ የፓርላማ ልኡካን ቡድኑ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

የፈረንሳይ ልኡካን ቡድኑ መሪ ሀበር ላፈርኒ በኩላቸው የፈረንሳይ ፓርላማ በአገር አቀፍ ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች ላይ ጥሩ ልምድ ያለው መሆኑን አብራርተው ይህንኑ ልምድ ለማካፈልና የፓርላማ ቡድንን የአመራር ብቃት ለማሳደግ ከኢትዮጵያ ፓርላማ አባላት ጋር በጋራ እንደሚሰሩ ነው የተጠቆመው፡፡

ልኡካን ቡድኑ የኢትዮጵያ የጤና ፖሊሲ ምን ለውጥ እንዳመጣ፣ መንግስት ምን ያህል ትኩረት ሰጥቶ እንደሚከታተለው ማብራሪያ የጠየቀ ሲሆን፤ ቋሚ ኮሚቴዎቹ በበኩላቸው በአገሪቱ የጤና በጀት አጠቃቀም፣ የጤና ልማት ፕሮግራሞችን ከማሳደግ፣ እናቶችና ህጻናት ሞትን ከመቀነስ እንዲሁም ጤናማ ህብረተሰብን ከማፍራት አኳያ ፓርላማው ተገቢውን ክትትልና ቁጥጥር እንደሚያደርግ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

የሁለቱን አገራት የእርስበርስ ግኑኝነት ለማጠናከር በእድገት ዘርፍ በዋናነትም በጤናው በኩል የሚደረገውን እንቅስቃሴ በማሳለጥ ረገድ በውጤታማ አፈጻፀም ከተያዙ አገራት ኢትዮጵያ ግንባር ቀደም መሆኗ በውይይቱ የተገለጸ ሲሆን፤ ከአውሮፓ አገራት መካከል ፈረንሳይ ከኢትዮጵያ ጋር የቆየ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ያላት ከመሆኑም ጋር ተያይዞ ይህንን ተግባር ይበልጥ ለማጠናከር በቀጣይ በጋራ እንደሚሰሩና ፈረንሳይ የምታደርገው ድጋፍም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ግብዛቤ ተይዟል፡፡