null China, Ethiopia parliamentary cooperation

 በኢትዮጵያና ቻይና መካከል ያለውን የኢኮኖሚ ትብብር ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የኢትዮጵያ ፓርላማና የቻይና ብሔራዊ ኮንግረስ የበኩላቸውን ሚና ሊወጡ ይገባል ሲሉ የሕ/ ተ/ም/ ቤት አፈ-ጉባኤ ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ገለፁ።

የሕ/ ተ/ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ  ክብርት  ወ/ሮ  ኬሪያ ኢብራሂም  ለ3 ቀናት በኢትዮጵያ ጉብኝት እያደረጉ ያሉትን የቻይና ብሔራዌ ኮንግረስ አፈ- ጉባኤው ሚስተር ሊ ዛንሽን ተቀብለው አነጋግረዋል፤

ሚስተር ሊ ዛንሽን ከሁለቱ ምክር ቤት አፈ-ጉባኤዎች ጋር በነበራቸው ቆይታ  የሁለቱ  አገራት ምክር ቤቶች የፓርላማ ሁለትዮሽ ግንኙነት መጠናከር ላይ  እና የሁለቱን አገራት  የቆየ የኢኮኖሚ ትብብር  ወደ ላቀ ደረጃ በሚያሸጋግሩ ጉዳዮች ላይ መክረዋል።

ሚስተር ሊ ዛንሽን እንደገለፁት  በአሁን ወቅት የኢትዮጵያና ቻይና ግንኙነት በአዲስ ምዕራፍ የሚገኝ ሲሆን፤ የእሳቸው የኢትዮጵያ ጉብኝትም አገራቸው ለአዲሱ የአገሪቱ መንግስትን ለመደገፍ ፍላጎቷን ያሳየችበት ነው ሲሉ ተደምጠዋል፤ ቻይና ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እድገት በመሰረተ ልማት፣ በአቅም ግንባታና በአምራች  ኢንዱስትሪው ዘርፍ እያደረገችው ያለውን ድጋፍ አጠናካራ ትቀጥላለች ነው ያሉት፤በኢትዮጵያ የተደረገው ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር የፖለቲካ አመራሩን የፖለቲካ ብስለትና  አቅምን የሚያሳይነው ብለዋል ሚስተር ሊ ዛንሽ በንግራቸው፤

ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በበኩላቸው  ሁለቱ አገራት  ቀደምት የስልጣን ባለቤት መሆናቸውን አንስተው  ኢትዮጵያ እየገጠሟት ያሉ የልማት  ፈተናዎች ከቻይና ጋር የሚያመሳስላት ነው ብለዋል፤ በመሆኑም ከአገሪቱ  ነባራዊ  ሁኔታ ጋር የተጣጣመ የቻይናን የልማት መስመር እንደምትከተል ገልፀው፤ ቻይና የኢትዮጵያ ግንባር ቀደም የልማት አጋር  እንደመሆኗ የልማት ትስስሩን ይበልጥ እንዲጠናከርና ለዚህም ስኬት የሁለቱ አገራት ምክር ቤቶች ከምንግዜውም በላይ በቅርበት ሊሰሩ እንደሚገባ አሳስበዋል፤

 የፖለቲካ ጥቅሞቻቸውንም ለማስጠበቅ እና ኢትዮጵያ  ለምሰራቅ አፍሪካ  ቀጠና የፓለቲካ  መረጋጋትና የፀጥታ  መረጋገጥ ለምታደገው ጥረት የቻይና ድጋፍ ወሳኝ መሆኑን አስገንዝበዋል፤

በውይይቱ መጨረሻም የመግባቢያ ሰነድ የፈረሙ ሲሆን የምክር ቤቶቹን ግንኙነት ለማጠናከር እድል የሚፈጥር ነው ተብሏል።