null Committee of the House reported that the awash arba dullecha road constraction is delayed.

የአዋሽ አርባ ዱለቻ መንገድ ግንባታ መጓተቱን በስፍራው የመስክ ምልታ ያደረገው ቋሚ ኮሚቴ ገለፀ፤

በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የግብርና፣ አርብቶ አደርና አከባቢ ጥበቃ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በአዋሽ አርባ ዱለቻ መንገድ ግንባታ ጉብኝት አድርጓል፡፡

በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን የፕሮጀክቱ ኃላፊ / ፀጋዬ መኮንን 53 ኪሎ ሜትር ርቀት ያለው የአዋሽ አርባ ዱለቻ መንገድ ስራ በእ.. 2016 ሰኔ የተጀመረ ሲሆን፤ፕሮጀክቱ 816 ቋሚና የቀን ሰራተኞች ይዟል፤ የመንገድ ስራው ሰራተኞች በአብዛኛው የአከባቢው ነዋሪዎች ሲሆኑ የመንገድ ፕሮጀክቱ የስራ ዕድል  ተጠቃሚ እያረጋቸው  ይገኛል፡፡

/ሩም አክለው በተለይ የሴቶች ተጠቃሚነት በአሚባራ ወረዳ ላይ ከጊዜ ወደ ጊዜ ከፍተኛ እየሆ መምጣቱንም የሚያስደስት ተግባር ቢሆንም ሰራተኞች የደህንነት ልብሳቸውንና አስፈላጊውን ጥቅማጥቅም ከማሟላት ረገድ አልፎ አልፎ ጉድለት እንዳለ እንዲሁም በስራዎች መቆራረጥ የትርፍ ጊዜ ክፍያ እያገኙ ባለመሆናቸው ቅሬታ እያስነሳ ነው፡፡

ቋሚ ኮሚቴው በምልከታው ወቅትም የመንገዶች መስፋፋት የአርብቶ አደሩን ጥቅም ከማጉላት ታቅዶና መሰራቱ መልካም ሆኖ ሳለ ፕሮጀክቱ ከታቀደው በላይ ጊዜ በመውሰድ የመጓተት ሂደቱ እንደ ድክመት አንስቷል፡፡

የፕሮጀክቱ ኃላፊዎችም ለችግሩ መዘግየት ምክንያት  የግብዓት ዕጥረት፣ የበጀትና ከወሰን ማስከበር ጋር ተያይዞ ከአከባው ነዋሪዎች ጋር ባለመግባባት በመፈጠሩ እንደሆነ ተናግረው በተፈጠረው ችግርም ድርጅቱ ለከፍተኛ ወጪ እየተዳረገ  ነው ብለዋል፡፡

በሌላ በኩልም በዱለቻ ወረዳ በኩል 10 ኪሎ ሜትር ረግረጋማ መሬት በመሆኑ ለመስራት ከባድና በርካታ ጊዜም የወሰደ ሲሆን በአከባቢው ካሳው ተከፍሎ ከስፍራው ያልተነሱ አርብቶ አደሮች በመኖራቸው ለስራው እንቅፋት እንደሆነም ነው አክለው ለቋሚ ኮሚቴው አስገንዝበዋል፡፡

ኮርፖሬሽኑ በርካታ ሳይቶች ካሉት ኋላ የቀረና ልዩ ትኩረት ይሰጠዋል ተብሎ ከተቀመጡ የአዋሽ አርባ ዱለቻ መንገድ አንዱ ቢሆነም እስካሁን ምንም የተለየ ድጋፍ እያገኙ እንዳልሆነ ብሎም በነዳጅና ተሸከርካሪ ዕጥረት የስራው መቆራረጥ ቀጥሏል ነው የተባለው፡፡