null Defense Force members should participate in a peaceful nationwide examination to be completed peacefully.

ስጋት ባለባቸው አካባቢዎች ለሚሰጠው ሃገር አቀፍ ፈተና ሰላማዊ በሆነ መልኩ እንዲጠናቀቅ መከላከያ ሰራዊት መሳተፍ እንዳለበት ተገለፀ

የሃገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ የፀጥታ ስጋት ባለባቸው አካባቢዎች ለሚሰጠው ሃገር አቀፍ ብሄራዊ ፈተና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት መስራት እንዳለበት የሰው ሃብትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አሳስቧል፡፡

ግንቦት 12/2011 . በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሃብትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በወቅታዊ ሃገር አቀፍ የፈተና ዝግጅትና ተያያዥ ጉዳዮችን አስመልክቶ የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር / ጥላዬ ጌቴን ጨምሮ ከኤጀንሲው የስራ ኃላፊዎች ጋር ተወያይቷል፡፡

የጸጥታ ስጋት ባለባቸው አካባቢዎች ለሚሰጠው ሃገር አቀፍ ብሄራዊ ፈተና ኤጀንሲው በምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ትኩረት አድርገው ተወያይተዋል፡፡

ከአካባቢው የጸጥታ አካላትና አመራሮች ጋርም በቅንጅት እየተሰራ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

ፈተናውን ለመስጠት ያሉ አስጊ ሁኔታዎች በዝርዝር ተተንትነው የተለዩ ሲሆን፤ ኮማንድ ፖስት ተመስርቶ እስከ ወረዳ መዋቅር ድረስ የዘለቀ ስራ እየተሰራ እንደሆነም ሚኒስትሩ አክለዋል፡፡

ሰሞኑን በአንዳንድ አካባቢዎች ላይ የመምህራን አድማ ማድረግ ፈተናውን እንዳያስተጓጉለው ምን ሊሰራ ታስቧል የሚል ጥያቄ ከምክር ቤት አባል ተነስቷል፡፡

አድማው መምህራኑ የጠየቁት ጥያቄ ሙሉ ለሙሉ ባለመመለሱ የተከሰተ እንደሆነ / ጥላዬ ጠቅሰው ከአድማው ጋር ተያይዞ ፈተናው ችግር ላይ እንዳይወድቅ የብሄራዊ መረጃና ደህንነትን ጨምሮ ከክልል አመራሮች ጋር በቅርበት እየተሰራ እንደሆነ አብራርተዋል፡፡

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ምደባን በተመለከተ ፍትሃዊ ህብረ-ብሄራዊ ስብጥርና ግልጽነት እንዲኖረው ከማድረግ አንጻር ቋሚ ኮሚቴው ባደረገው የመስክ ምልከታ ውስንነቶች መኖራቸውን በማረጋገጡ ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት ምን የታሰበ ነገር አለ ሲልም ቋሚ ኮሚቴው አክሎ ጠይቋል፡፡

ከምደባው ጋር ተያይዞ በቋሚ ኮሚቴው በኩል የተነሳውን ጥያቄ በቀጣይ ወስደው እንደሚሰሩበት የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ አርዓያ /እግዚአብሄር ገልጸዋል፡፡

በቅርቡ በሚሰጠው ሃገር አቀፍ ፈተና ኩረጃ የፀጥታ ስጋት እንዳይሆን ኤጀንሲው በትኩረት መንቀሳቀስ እንዳለበት በሰው ሃብት እና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የአጠቃላይ ትምህርት ንዑስ ሰብሳቢ / ራቢያ ኢሳ ጠቁመዋል፡፡

ፈተናው ሰላማዊ በሆነ መንገድ እንዲጠናቀቅ የምክር ቤቱ የውጭ ግንኙነትና ሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ድጋፍ እንዲያደርግላቸው / ጥላዬ ጠይቀዋል፡፡