null It is working to prevent physical and psychological abuse of detainees.

በታራሚዎች ላይ ሲፈጸም የነበረውን አካላዊና ስነ-ልቦናዊ የመብት ጥሰቶች ለማስቀረት የፌደራል ማረሚያ ቤቶች  እየሰራ መሆኑን  ቋሚ ኮሚቴው ገለጸ፡፡

ጥቅምት 14 ፣ 2012 ዓ.ም ፤  በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕግ ፍትህና ዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ  ኮሚቴ  በታራሚዎች ላይ ሲፈጸም የነበረውን አካላዊና ስነ-ልቦናዊ የመብት ጥሰቶች ለማስቀረት የፌደራል ማረሚያ ቤቶች   እየሰራ መሆኑን ባዘጋጀው የአስረጅዎች መድረክ  ላይ  ገልጿል፡፡

ቋሚ ኮሚቴው የታራሚዎችን ሁለንተናዊ  አያያዝ ለማሻሻል በቀረበው ረቂቅ አዋጅ ዙሪያ ከፌደራል ማረሚያ ቤቶች የስራ ኃላፊዎች  ጋር ሲመክር ውሏል፡፡

የሰብዓዊ መብት አያያዝን አስመልክቶ በፌደራል ማረሚያ ቤቶችና በፌደራል ጠቅላይ አቃቢ ህግ በኩል በ2010 ዓ.ም መጨረሻ ላይ የዳሰሳ ጥናት መካሄዱን የፌደራል ማረሚያ ቤቶች ዋና ዳይሬክተር አቶ ጀማል አባሶ ተናግረዋል ፡፡

በተደረገው ጥናት ላይ ተመስርቶ የተገኙ ግኝቶችን  በወንጀል ፍትህ አስተዳደር ማሻሻያ የባለሙያዎች ቡድን፣ በኢትዮጵያ ህግ ባለሙያዎች ፣ በአለም አቀፍ ቀይ መስቀልና በሌሎች ባለድርሻ አካላት ታይቶና ግብዓት ተሰብስቦ አስተያየት እንደተሰጠበት ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡

የአዋጁ መሻሻል ታራሚዎች በማረሚያ ቤት ቆይታቸው የእውቀትና የሙያ ባለቤት እንዲሆኑ በማስቻልና ተደጋጋሚ  ወንጀልን ለማስቀረት እንደሆነም ዳይሬክተሩ ጠቅሰዋል፡፡  

በተጨማሪም  ታራሚው በማረሚያ ቤት ቆይታው በማረሚያ ቤት ሰራተኞች ላይ  ጉዳት ለማድረስ የሚገመተውን የስጋት ደረጃ በመወሰን የእርምት ተግባሩን ሊለውጥና ሊያሻሽል  እንደሚችልም አቶ ጀማል አስረድተዋል፡፡

ሲስተዋሉ የነበሩት ችግሮችን ታሳቢ ተደርጎ ረቂቅ አዋጁ እንዲሻሻል የተሄደበትን ርቀት የቋሚ ኮሚቴው ተወካይ  ወ/ሮ የሺዕመቤት ነጋሽ በጥንካሬ ጠቅሰዋል፡፡