null Participation of stakeholders in the Ministry of Women, Children and Youth is low.

የሴቶች፣ ህጸናትና ወጣቶች ሚንስቴር ሴቶችንና ወጣቶችን ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት ከማድረግ አኳያ አፈፃጸሙ ዝቅተኛ ነው ተባለ፡፡                                                                          

መጋቢት 27 ቀን 2011 ዓ.ም 5ኛው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ መት የስራ ዘመን ባካሄደው 4ኛ ልዩ ስብሰባ የሴቶች፣ ህጻናትና ወጣቶች ሚኒስቴርን በ8 ወራት ሪፖርት ካዳመጠ በኋላ የተሰሩትን ጠንካራና ደካማ ተግባራትን በዝርዝር ገምግሟል፡፡

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በበጀት ዓመቱ እቅድ ላይ የህዝብ ክንፍና ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍና እቅዱ ዳብሮ እንዲፀድቅና ወደ ፈጻሚ አካላት እንዲወርድ ተደርጎ ወደ ተግባር መግባቱ፣ የመስሪ ቤቱን አመራሮችና ፈጻሚዎችን የማስፈጸሚያና አቅማቸውን ለማጎልበት የተለያዩ ስልጠናዎች መሰጠታቸው፣ በሴቶችና በወጣቶች ዘርፍ የሴቶችን የቁጠባ ባህል ለማሳደግ የተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ መሰጠቱን ምክር ቤቱ በጥሩ ጎኑ አንስቷል፡፡

እንዲሁም የሴት ተማሪዎችን የትምህርት ተሳትፎና ውጤት ለማሳደግ በተለይ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ የኢኮኖሚ ችግር ያለባቸውን ሴት ተማሪዎች ተመርጠው ባለሀብቶችን በማፈላለግ ሴቶች ተጠቃሚ መደረጋቸውና ወጣቶች በተለያዩ በጎ ፍቃድ ስራዎች ላይ ለበርካታ የህብረተሰብ ክፍሎች አገልግሎት እንዲሰጡ ማድረጋቸው ጥሩ እንደሆና ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ሲሉ ቋሚ ኮሚቴ አባላት አንስተዋል፡፡

በሌላ በኩል በሴቶችና በወጣቶች ዘርፍ ላይ የሴቶች ኢኮኖሚ ተጠቃሚነትና ተሳታፊነት ለማሳደግ የመጣው ለውጥ እና በወጣቶች የግንዛቤ ስራ ኢኮኖሚ ተሳታፊነት የተሰራው ስራ ሲገመገም እጅግ ዝቅተኛ መሆኑ፣ ሚኒስተር መስሪያ ቤቱ በየተቋማቱ የሴቶችና የወጣቶች ተሳታፊነት ተጠቃሚነት ላይ የሚታዩ የአሰራር ችግሮችን ለይቶና ነቅሶ ከማውጣት አኳያ በርካታ ችግሮች መኖራቸውን በደካማ አፈፃፀም አስቀምጧል፡፡

የሴቶች፣ ህጻናትና ወጣቶች ሚኒስቴር ሚኒስትር ወ/ሮ ያለም ጸጋይ በበኩላቸው የቋሚ ኮሚቴውና የምክር ቤቱ አባላት ያነሷቸውን ጥያቄዎችንና አስተያየቶች ተቀብለው እንደግብዓት እንደሚወስዷቸው ከጠቆሙ በኋላ የሴቶችን ተጠቃሚነትና ተሳታፊነት ከማረጋገጥ አኳያ በህገ-መንግስቱ መሰረት ሁሉም ተስተካሎ እንዲሰራ መመሪያዎችና ፖሊሲዎች ስላሉ በዚህ ዓመት ሴቶችን በኢኮኖሚ ተጠቃሚ ለማድረግ አንድ ኮሚቴ ተቋቁሞ ችግሮች ተለይተው በሰነድ መቀመጣቸውን፣ ችግሮቹን ለመፍታትም ከሚመለከተው መስሪያ ቤቶች ጋር የጋራ መድረክ በመፍጠር ውይይት መደረጉንና በዚህ ዓመት 60 ሚሊዮን በጀት ተመድቦ ለሴቶች ድጋፍ እንደተደረገላቸው ሚኒስቴሯ ጠቅሰዋል፡፡

የቋሚ ኮሚቴው ንዑስ ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ አለሙ ገብሬ በሪፖርቱ ላይ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ብቻ የተከናወኑትንና ያሉትን ችግሮች ለይቶ ባለማስቀመጡና በዚህ ከቀጠለ የሴቶችንና የወጣቶችን ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ይቻላል ብሎ ቋሚ ኮሚቴው እንደማያምንና መንግስትም ልዩ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

አክለውም በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሊሰሩ የሚገባቸውን ተግባራት ተለይተው ያልቀረቡ ስለሆነ ተለይተው መቀመጥ እንዳለባቸውና በተጨባጭ መሬት ላይ ያሉስራዎች ምን እንደሚመስሉ ወርዶ ማየትና የማስተካከያ እርምጃዎችን መውሰድ እንዳለበት፣ ቋሚ ኮሚቴው ለሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በሁሉም ሩብ ዓመታት የሚሰጠውን ግብረ መልስ ተቀብሎ አለመጠቀም ችግር እንዳለና አለመግባቶችም እየተፈጠሩ ስለሆነ በቀጣይ በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባም ነው ያስረዱት፡፡

በቀጣይም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከቋሚ ኮሚቴውና ከምክር ቤት አባላት የተሰጡትን አስተያየቶች በግብዓትነት በመውሰድ የሴቶችና ወጣቶች ተሳታፊነት፣ ተጠቃሚነትና እንዲሁም ለህጻናት መብትና ደህንነት የበለጠ ተጠናክሮ መሰራት እንዳለበትም የተከበሩ አቶ አለሙ ገብሬ አስገንዝበዋል፡፡