null Poor Project Management system caused extravagancy in the construction sectors.

በፕሮጀክት ማኔጅመንት አሰራር ስርዓት ላይ ወጥነት አለመኖር የኮንስትራክሽን ዘርፍ በሚፈለገው ልክ እንዳያድግ እና ለብክነት እንዲጋለጥ አድርጓል ተባለ፡፡

ከተማ ልማት፤ ኮኒስትራክሽን እና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴው የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ፕሮጀክት ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት የ6 ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርትን ገምግሟል፡፡

 በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው መሰረታዊ ለውጥ በማምጣት ፈጣን ልማትን በማስቀጠል ተወዳዳሪ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ለመፍጠር የሚያስችል ፖሊሲ ተግባራዊ በማድረግ፤ የፕሮጀክቶች አፈጻጸም አቅም ግንባታን በመፍጠር፤ የቴክኖሎጂ ሽግግር ስራዎችን እና የማማከር አገልግሎት በመስጠት የበኩሉን እየተወጣ እንደሆነ የኢንስቲትዩት አመራሮች ገልጸዋል፡፡

ኢንስቲትዩቱ የተቋቋመበትን ዓላማ ለማሳካት በዘርፉ እየታዩ ያሉትን ችግሮችን በጥናትና ምርምር ስራዎች የተደገፉ ውጤቶችን እንዲያመጡ ለይቶ በማውጣት መሪ ሃሳቦችን በመስጠትና የሰው ሃይልን በዕውቀት ለማዳበር ለዘርፉ ዕድገት በርካታ ስራዎችን እየሰራ እንደሆነም ጠቅሰዋል፡፡

ቋሚ ኮሚቴው ኢንስቲትዩቱ ግንባታዎችን ከጊዜ፣ ከወጪና ከጥራት አንጻር የተሸሉ በመሆን የመንግስትን ሀብት በአግባቡ ስራ ላይ ኢንድውል የሚያስችል ወጥ እና ዘመናዊ የፕሮጀክት ማኔጅመንት አሰራር ስርዓቶችን ለማስፈን የሚያስችል አሰራር እስካሁን ተግባራዊ ሳይሆን ለብዙ ጊዜ መጓተቱ የኢንስቲትዩቱን አፈጻጸም ዝቅተኛ ከማድረጉም ባሻገር መንግስትን ለወጪ እየዳረገ መሆኑን አንስቷል፡፡

ቋሚ ኮሚቴውም ኢንስቲትዩቱ ባለፉት ጊዜያት በሰው ሃይልና በቴክኖሎጂ ሽግግር እንዲኖር ለማድረግ ከሀገር ውስጥም ሆነ ከውጭ የቀመራቸውን የተለያዩ ልምዶችን ለተቋሙም ሆነ ለኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው ፋይዳ ባለው መልክ ግብዓት እንዲሆን ተደርጎ የተለያዩ ስራዎችን ቢሰሩም ችግሩን ከመፍታት አኳያ ቀጣይ ስራ የሚጠይቅ እንደሆነ ቋሚ ኮሚቴው ገምግሟል፡፡

ኢንስቲትዩቱ በበኩሉ በግንባታው ረገድ በተለይም በመንገድ ግንባታ፣ በባቡር ሃዲድ ዝርጋታ እና በህንጻ ግንባታውም ዙሪያ ልምዶችን ከጀርመንና ቱርክ አገራት በመቅሰም አሁን ስራ ላይ በማዋል ውጤቶችን እያመጡ እንደሆነ ነው፡፡

ቋሚ ኮሚቴው በኢንስቲትዩቱ በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች እና ፈጻሚዎችን በተገቢው አለመምራት፣ የታታሪነት፣ ተልዕኮን መሸሽ፣ ከስራ ገበታ መቅረትና በመንግስት ስራ ሰዓት በቢሮ ውስጥ የግል ስራ መስራት የተለዩ ችግሮች እንደሆኑ በሪፖርቱ የተመላከተ ሲሆን ኢንስቲትዩት አመራች በበኩላቸው ችግሮቹን በመቅረፍ ላይ እነዳለ ነው ምላሽ የሰጡት፡፡

በመጨረሻም ቋሚ ኮሚቴው ኢንስቲትዩቱ  ለዘርፉ ዕድገት ከፍተኛ ሚና ያለው በመሆኑ ከምንም በላይ መንግስትን ለወጪ የሚዳርጉትን ለይቶ በጥናት በማሰደገፍ ችግሮችን ለመቅረፍ ጠንክሮ መስራት እንዳለበት እና ከቋሚ ኮሚቴው የተሰጡ ግብረ-መልሶችን ከመከላከል ይልቅ አጋዥ አድርጎ ድክመቶችን ተቀብሎ ለማረም መጣር እንዳለበት ጭምር አሳስቧል፡፡