null Speaker of the House of People's Representatives, Hon. Ato Tagesse Chafo, gave a press release on the 2019 performance of the House.

የኢ.ፌ.ድ.ሪ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ የተከበሩ አቶ ታገሰ ጫፎ  የምክር ቤቱን የ2011 በጀት ዓመት አፈጻጸምን በተመለከተ   ለጋዜጠኞች  መግለጫ ሰጡ፡፡

 ዜና ፓርላማ ቀን 4/11/2011 ዓ.ም፡- የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት  በዋናነት ሕግ ማውጣት፣ ህግ ማስፈጸምና የውክልና ተግባራትን ያከናውናል፡፡ ም/ቤቱ በሥሩ ቀደም ሲል 21  ቋሚ ኮሚቴዎች እንደነበሩት አፈ-ጉባኤው አስታውሰው፡  በበጀት አመቱ አደረጃጀቱን በማሻሻል 10 ቋሚ ኮሚቴዎች እና  33 ንዑስ  ኮሚቴዎች በሥሩ በማካተት ተጠሪ ለሆኑ ተቋማት ተገቢውን ድጋፍና ክትትል ማድረጋቸውን ለጋዜጠኞች ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

ቋሚ ኮሚቴው  የሰው ሀይሉን በማደራጀት አኳያ በተለይ የመስክ ምልከታ በሚደረግበት ጊዜ በዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ትኩረት  አድርጎ  ሲሰራ  መቆየቱን አቶ ታገሰ ጠቅሰው የሚወጡ አዋጆች ወቅታዊነታቸውን በማየት እንደ ጸረ-ሽብርና የጦር መሳሪያ አዋጅ በከፍተኛ ደረጃ ክርክርና ውይይት እንደተደረገባቸውና እስካሁን የወጡት ህጎች ተፈጻሚነታቸውና  ኦዲት አንደሚደረግም ተናግረዋል፡፡

በ2011 በጀት ዓመት 67 አዋጆች ለቋሚ ኮሚቴው ቀርበው 62ቱን በመመርመር በምክር ቤቱ ጸድቀው ተግባራዊ በመደረግ ላይ ናቸው፡፡ በተጨማሪም 2 ደንቦች  መጽደቃቸውን አቶ ታገሰ ገልጸው ቀጣይም ህግ ከማውጣት አኳያ አንገብጋቢና ወሳኝ ስራዎችን ሊያሰሩ የሚችሉ ህጎችን ትኩረት አድርገው ለመስራት በዝግጅት ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

አስፈጻሚ ተቋማት ምን ያህል እየሰሩ እንደሆነ ቋሚ ኮሚቴዎች በየዘርፋቸው ቁጥጥርና ክትትል አድርገዋል፡፡ ሁሉም ቋሚ ኮሚቴ የአስፈጻሚ ተቋማንት ሪፖርት  በየ ሩብ ዓመቱ የመስክ ምልከታን ጨምሮ የሚቀርቡ ሪፖርቶችን እየገመገሙ ግብረ -መልስ  ሲሰጡ እንደቆዩም አፈ-ጉባኤው አስረድተረዋል፡፡

ኦዲትን በተመለከተም ችግር ያለባቸውን ተቋማት በተለይ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከዋና ኦዲተር ጋር በመሆን በዩኒቨርስቲዎች ውስጥ የበጀት አጠቃቀም ላይ  የማስተካከያ ስራዎች እንደተሰሩና የአገር መከላከያ በሚያደርገው  ግዥም ግልጽነት በተላበሰ መልኩ እንደተሰራም አቶ ታጋሰ በመግለጫቸው ጠቁመዋል፡፡

አገሪቱ በአህጉር እና በአለም አቀፍ የፓርላማ አባል ከሆነችበት መድረክ   የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፓርላማ  ዲሞክራሲ የወዳጅነት ስራ ሲሰራ እንደቆየና ቀጣይም አሁን በአገሪቱ ያለውን ለውጥ እንዲደግፉ እቅድ በማውጣት እንቅስቃሴ መጀመሩን አፈ-ጉባኤው ለጋዜጠኞች አስገንዝበዋል፡፡

የዘንድሮው የፓርላማ  ክርክር ካለፉት  ጊዜያት በይዘቱ ለየት የሚያደርገው  በአጀንዳዎች ላይ  ሁሉም የምክር ቤት አባላት ያመኑበትን እና የተጣለባቸውን ሃላፊነት ለመወጣት በሚያስችል ደረጃ ምክንያታዊ ክርክር በማድረግ ሚናቸዉን በሚገባ እየተወጡ በመሆኑ ሊበረታታና ቀጣይነት ሊኖረው እንደሚገባም ነው አቶ ታገሰ የተናገሩት፡፡

በሃገሪቱ የተጀመረውን ሪፎርም ለማስቀጠል ቀጣይ በሚኖረው አንድ ዓመት የሪፎርም ፕሮግራም ዶክመንት በማዘጋጀት  የተለያዩ ምሁራንና የፓርላማ አባላት የሚሳተፉበት መድረክ በመፍጠር ህዝቡን ለማርካት ተቋማት ሊያሻሽሉ የሚገባቸውን ድክመቶች ለይተው በማስቀመጥ  የፓርላማ ዲሞክራሲ አሰራር ሂደቶች ተለይተው የድርጊት መርሃ ግብር በዝግጅት ላይ መሆኑን አፈ-ጉባኤው ለጋዜጠኞች አስረድተዋል፡፡

በ2012 በጀት ዓመትም አስፈጻሚ ተቋማት  ህብረተሰቡ የሚያነሳቸውን ወሳኝ  ጉዳዮችን በመለየትና በማጤን መድረክ በማዘጋጀት  በተለይ የኑሮ ውድነትና የዋጋ ግሽበትን እንደሁም የህብረተሰቡን ማህበራዊ ኑሮ የሚዳስሱና መሰለ ችግሮች ላይ ያተኮረ የጥያቄና መልስ ውይይት እንደሚደረግም አቶ ታገሰ በመግለጫቸው ጠቁመዋል፡፡

በመጨረሻ አቶ ታገሰ ጫፎ  በጋዜጠኞች ለተነሳላቸው ጥያቄዎች መልስና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡