null The Ethiopian Commodity Exchange should modernize its exchange systems.

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ የአርሶ አደሩን የምርት ተጠቃሚነት ለማሳደግ ዘመናዊ የግብይት ስርአቱን የበለጠ ማሳደግ እንዳለበት የንግድና ኢንዱስትሪ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አሳሰበ፡፡        

ቋሚ ኮሚቴው ዛሬ መጋቢት 13 ቀን 2011 ዓ.ም የኢትዮጵያ ምርት ገበያን ዘመናዊ የግብይይት ስርዓትና የቡና ናሙና ላብራቶሪውን የስራ እንቅስቃሴ በአካል ተገኝቶ ጎብኝቷል፡፡

በጉብኝቱ ወቅት የኮርፖሬት ኮሚኒዩኬሽን ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ነፃነት ተስፋዬ ስለ ተቋሙ እንቅቃሴ አጠር ያለ ማብራሪያ ያቀረቡት ሲሆን ተቋሙ ከጊዜ ወደ የግብይይት ስርዓቱን እያዘመነ፣ አዳዲስ ምርቶችን ወደ ገበያ በማስገባት እና የግብይት ማዕከላትን በመክፈት ተደራሽነቱን እያሰፋ መምጣቱን አብራርተዋል፡፡

አርሶ አደሩ ለደላሎች ሳይጋለጥ ምርቱን በቀጥታ ለማዕከሉ እንዲያቀርብ በአራት ቋንቋዎች በ929 እና በ934፣ በ14 የተለያዩ የፌደራልና የክልል ሚዲያዎች፣ በማዕከሉ ዌብ ሳይት እንዲሁም በማህበራዊ ሚዲያዎች መረጃ እንዲያገኝ በማድረግ በዋጋ የመደራደር አቅሙን የማሳደግ ስራ እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

አክለውም ከባንኮች ጋር በትስስር በመስራት አርሶ አደሩ የምርቱን ሽያጭ በፍጥነት እንዲገኝ እየተደረገ እና በቀጣም ምርቱን አሲዞ የብድር አገልግሎት የሚገኝበት ሁኔታ እየተመቻቸ ነውም ብለዋል፡፡

የቋሚ ኮሚቴ አባላትም የገዥና ሻጭ ማገበያያ እና የቡና ናሙና ላብራቶሪን ተዟዙረው በጎበኙበት ወቅትም የተለያዩ ጥያቄዎችን አንስተው በሃላፊዎቹ ማብራሪ የተሰጠ ሲሆን፣ ግብይይቱ ከሰው ንክኪ ነፃ፣ በግልፅ መረጃ ላይ የተመሰረተ፣ በኤሌክትሮኒክስ የታገዘና በካሜራ ክትትል የሚደረግበት መሆኑ ተብራርቷል፡፡

የቡና ላብራቶሪው አለማቀፍ ደረጃውን የጠበቀ፣ አገሪቱ ጥራት ያለው ምርት ለአለም ገበያ እንድታቀርብ የሚረዳና ናሙናውን ሲፈተሽ ኮድ እየተሰጠው በመሆኑ ከንክኪና አድሎ ነጸ ነውም ነው የተባለው፡፡      

በመጨረሻም የንግድና ኢንዱስትሪ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ ጌታቸው መለሰ የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ተደራሽነቱን እያሰፋና የግብይይት ስርዓቱን እያዘመነ መምቱን፣ አርሶ አደሩ ወቅታዊ የዋጋ መረጃ እንዲገኝ፣ እንደ ስንዴና ገብስ የመሳሰሉት ምርቶች ወደ ግብይይት እንዲገቡ መደረጉን፣ አርሶ አደሩ ከዚህ በፊት ያጋጥመው ከነበው ደረቅ ቼክ ተላቆ የምርቱን ሽያጭ ገንዘብ ከባንኮች ወዲያው እንዲገኝ መደረጉን እና  የላብራቶሪውን የስራ እንቅስቃሴን በጠንካራ አፈፃጸም አንስተዋል፡፡

በሌላ በኩል ተቋሙ በቀጣይ የራሱ ህንፃና መጋዘን የሚገነባበት ሁኔታ መፍጠር እንዳለበት፣ የግብይይት ሥርዓቱን የበለጠ ማዘመንና በአለም ገበያ ግብይይት በቀጥታ ተሳታፊ የመሆን እንዲሁም አርሶ አደሩ ምርቱን አሲዞ የብድር አገልግሎት እንዲያገኝ የማድረጉ ስራ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም አሳስበዋል፡፡